በፓሪስ አፍጋናዊው በስለት 7 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

በፓሪስ አፍጋኒስታናዊው በስለት 7 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ Image copyright Reuters

በፈረንሳይዋ መዲና ፓሪስ ስለት እና ፌሮ ብረት በመጠቀም ጥቃት ያደረሰው አፍጋኒስታናዊ 7 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ።

የፈረንሳይ ፖሊስ እንዳለው 4ቱ በጽኑ ተጎድተዋል።

አፍጋኒስታናዊ ዜግነት ያለው ጥቃት አድራሽ በቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ፖሊስ ጨምሮ አስታውቋል። ጥቃቱ የሽብር ጥቃት ስለመሆኑ ምንም ፍንጭ የለም ተብሏል።

ጉዳት ካስተናገዱት መካከል ሁለቱ እንግሊዛዊያን ናቸው።

በማዳጋስካር ስታድየም ሰዎች ተረጋግጠው ሞቱ

በደቡብ ሱዳን አውሮፕላን ተከስክሶ '19 ሰዎች ሞቱ'

ነውጥ በፓሪስ ከተማ

የዓይን እማኞች እንደሚሉት ከሆነ ጥቃት አድራሹ በመንገድ ላይ የነበሩ ሁለት ወንዶችን እና አንዲት ሴትን በስለት ወግቷል።

በአካባቢው የነበሩ ሌሎች ሰዎች ጥቃት አድራሹ ላይ የተለያዩ ቁሶችን በመወርወር ከአካባቢው እንዲሸሽ አስገድደውት ነበር።

ጥቃት አድራሹም ከአካባቢው ከሸሸ በኋላ በመንገዱ ላይ ያገኛቸው ሁለት የእንግሊዝ ሃገር ጎብኚዎች ላይ ጥቃት አድርሷል።