የሰኞ ምሽት አጫጭር ዜናዎች

አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ

ኢትዮጵያ

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ)እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በጋራ ለመስራት ግንዛቤ ላይ መድረሳቸውን ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታወቁ።

ድርጅቶቹ የኦሮሞና የኦሮሚያ ጥቅም ስለሚከበርበት ሂደት የጋራ ግንዛቤ ላይ መድረሳቸውም በመግለጫው ላይ ተመልክቷል።

በሌላ የኢትዮጵያ ዜና

በመቀሌ ከተማ የሚገኙና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በያዝነው የትምህርት ዘመን ከክልሉ ዉጪ ወዳሉት ዩኒቨርሲቲዎች ለመሄድ ስጋት እንዳለባቸው ሰልፍ በማካሄድ ገለፁ።

ጉድዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው በትምህርት ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ ሃረጓ ማሞ ቀደም ብለው ከነበሩት ጊዜያቶች አገሪቷ በላቀ ሰላም ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰው የፌደራል መንግስት ለተማሪዎቹ ደህንነት አስፈላጊውን ጥበቃ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ሱዳን

የሱዳን ፕሬዚደንት በሽር አልአሳድ አገሪቱን እየተፈታተናት ያለውን የኢኮኖሚ ቀውስ ለማስታገስ በሚል የካቢኔ ቁጥራቸውን ቀነሱ።

ቀድሞ የነበራቸውን 31 ሚንስትሮች ቁጥርን ወደ 21 ዝቅ እንዲልም አድርገዋል።

ታንዛኒያ

የታንዛኒያው ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ በምስራቅ ታንዛኒያ ግዛት ሜሩ ባደረጉት ንግግር ጥንዶችን 'ብዙ ተባዙ' ሲሉ አሳሰቡ።

ፕሬዚደንቱ አውሮፓ በቤተሰብ ምጣኔ ሳቢያ ለህዝብ ቁጥር ማነስና ለአምራች ሃይል እጦት መዳረጓን ጠቅሰው 'የወሊድ መቆጣጠሪያን የሚጠቀሙ 'ሰነፍ ናቸው' ሲሉም ተደምጠዋል።

ሳዑዲ አረቢያ

ግብፃዊው የሆቴል ሰራተኛ ከሴት ባልደረባው ጋር ምግብ እየተመገቡ የተቀረፁት ተንቀሳቃሽ ምስል በመለቀቁ በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳረገ።

ምስሉ በተወሰነ መልኩ እጇና አይኗ የሚታይ ሴት ስታጎርሰውና እጃቸውን ለካሜራ ሲያውለበልቡ የሚያሳይ ነው።

ጤና

በመካካለኛ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች 'ከአልኮል ነፃ' የሚሆኑበት ቀናት ያስፈልጋቸዋል ሲል አንድ ጥናት ጠቆመ።

ይህንም ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘት፣ ክብደት ለመቀነስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊትና ካንሰር ለመከላከል እንደሚረዳ ሃኪሞች መክረዋል።

ከ45-65 የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በሌላ የእድሜ ክልል ከሚገኙት የበለጠ አልኮል ይጠቀማሉ።

ጃፓን

በትዊተር የተዋወቃቸውን 9 ሰዎችን በመግደል የተጠረጠረው ጃፓናዊ ክስ ተመሰረተበት።

ግድያውን የፈፀመው ወደመኖሪያ ህንፃው እንዲመጡ በማግባባት ገድሎና አካላቸውን ቆራርጦ በማቀዝቀዣና ሳትን ውስጥ አስቀምጦት እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል።

ፈረንሳይ

በፈረንሳይ ሰባት ሰዎችን በስለት በመውጋት ጉዳት ያደረሰው አፍጋናዊ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።

ጥቃቱ ከሽብር ድርጊት ጋር ስለመገናኘቱ ምንም ፍንጭ አልተገኘም።

አውስትራሊያ

ከ120 በላይ ኢንዶኔዥያውያን አውስትራሊያ ካሳ ልትከፍለን ይገባል ሲሉ ፊርማ እያሰባሰቡ ነው።

ግለሰቦቹ ህፃን እያለን በስህተት አዋቂዎች ናችሁ ተብለን በእስር ማቀናል ሲሉ ነበር ጥያቄያቸውን ያቀረቡት።

ለእስር የተዳረጉት በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ጥፋተኛ ተብለው ነበር።