«የወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፡- የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ማጉፉሊ

«ወሊድ መቆጣጠሪያን ወዲያ በሉት»፡- የታንዛኒያው ፕሬዝደንት ማጉፉሊ Image copyright AFP

የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሃገሪቱ በርካታ ሕዝብ ስለሚያስፈልጋት ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች መውሰድ ቢያቆሙ እንደሚሻል አሳውቀዋል።

«ሴቶች አሁን ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ ተስፋ ቢቆርጡ ይሻላል» ሲሉ ነው ማጉፉሊ የተደመጡት።

ተቃዋሚው የሕዝብ እንደራሴ ሴሲል ምዋምቤ የፕሬዚዳንቱ ሃሳብ ከሃገሪቱ የጤና ፖሊሲ ጋር የሚጣረስ ነው ሲሉ ማጉፉሊን ወርፈዋል።

የታንዛኒያ ሕዝብ 53 ሚሊዮን ገደማ የሚገመት ሲሆን፤ 49 በመቶ ያህሉ ዕለታዊ ገቢ ከ2 ዶላር (54 ብር ገደማ) በታች ነው።

አልፎም ሃገሪቱ ከዓለማችን ሃገራት ከፍተኛ የውልደት መጠን ያለባት ሃገር ናት፤ አንዲት ሴት በአማካይ አምስት ልጆች አላት።

ታንዛኒያ ቦይንግ "787-8 ድሪምላይነር" ገዛች

ማጉፉሊ ይህን በተናገሩ ማግስት የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፈ ቀላጤ የሆኑት ጆብ ዱጋይ ሴቶች ሰው ሰራሽ ጥፍር እና የዓይን ሽፋሽፍት እንዳይጠቀሙ ከልክለዋል።

ለቢቢሲ ድምፃቸውን የሰጡት አፈ ቀላጤው እገዳው ከጤና ጋር የተያያዘ ነው የሚል አጠር ያለ አስተያየት ሰጥተዋል።

አዲሱ ህግ ሴት የምክር ቤት አባላት ጉርድ ቀሚስና ጂንስ ሱሪ እንዳያደርጉ ያግዳል፤ ምክር ቤቱን የጎበኙ ሴቶችም ለህጉ ተገዢ እንዲሆኑ ይገደዳሉ።

ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ያደረጉት ማጉፉሊ «ሴቶች ብዙ ልጅ ወልደው እነሱን ለመመገብ ጠንክሮ ላለመሥራት ነው አንድ ወይም ሀሉት ልጅ ብቻ የሚወልዱት» ብለዋል።

በታንዛንያ አርግዘው የተገኙ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ታሰሩ

«ወደ አውሮጳ ተጉዤ ትንሽ ልጅ መውለድ ያለውን ጉዳት ተመልክቻለሁ» ሲሉም 'ልምዳቸውን' አካፍለዋል።

ተቃዋሚው ምዋምቤ «ማጉፉሊ ይህን ካሰቡ አራት የቤተሰብ አባል ብቻ የሚሸፍነውን የጤና ኢንሹራንስ ወደ አስር የቤተሰብ አባል ባሳደጉት ነበር» ብለዋል።

ማጉፉሊ፤ በፈረንጆቹ 2015 ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ስለ ወሊድ መቆጣጠሪያ ጉዳት ከመዘከር ቦዝነው አያውቁም።

ባለፈው ዓመት ነብሰ ጡር ተማሪዎች ከወለዱ በኋላ ትምህርት መቀጠል ባይችሉ የሚል ሃሳብ መስጠታቸው አይዘነጋም።

የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የሃሰት መረጃን ሊቆጣጠሩ ነው

ተያያዥ ርዕሶች