ከሴት ልጅ ጋር ማዕድ በመቅረቡ ለእስር የተዳረገው ግብጻዊ

ግብጻዊው እና የደሳውዲ ዜግነት ያለት ሴት አብረው ማዕድ ቀርበው
አጭር የምስል መግለጫ ይህን ማዕድ አብረው ከቀረቡ በኋላ ነበር ግለሰቡ ለእስር የተዳረገው

ግብጻዊው በሳውዲ አረቢያ ከአንዲት ሴት ጋር ቁርስ ሲመገብ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በትዊተር ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ለእስር ተዳረጓል።

ተንቀሳቃሽ ምስሉ የግብጽ የንግግር ዘዬ ያለው ግለሰብ የሳውዲ አረቢያ ዜጋ ነች ከተባለች ሙሉ ሂጃብ ከለበሰች ሴት ጋር ቁርስ ሲመገብ ያሳያል።

በሳውዲ ሕግ መሰረት በሥራ እና በመመገቢያ ቦታዎች ያላገቡ ሴቶች ካላገቡ ወንዶች ተነጥለው መቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

በጥቅም ላይ የዋሉ የጥንታዊ ግብፅ የህክምና ጥበባት

የሳውዲ ሴቶች በብዛት ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ ሲንቀሳቀሱ ወላጅ አባት፣ ባል፣ ወንድም ወይም ወንድ ልጃቸው አብሯቸው እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል።

ይህ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር የዋለው በሳውዲ መንግሥት ሲሆን ''በርካታ የሕግ ጥሰቶችን ፈጽሟል እንዲሁም ለሳውዲ ዜጎች ብቻ የተፈቀደ ቦታን ይዟል'' የሚሉ ክሶችም ቀርበውበታል።

ተንቀሳቃሽ ምስሉን ከ113 ሺ ጊዜ በላይ ሰዎች ተጋርተውታል።

በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሳውዲ ዜግነት አላት የተባለችው ሴት ከጎኗ ያለውን ወንድ ስታጎርሰው ይታያል።

በዚህም በርካታ የሳውዲ የትዊተር ተጠቃሚዎች በሁለቱ ግለሰቦች ድርጊት የተበሳጩ ሲሆን፤ በርካቶች ግን መቀጣት ያለባት እሷ እንጂ ግለሰቡ መሆን የለበትም እያሉ ነው።

ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አዲስ ሃሳብ አቀረበች

በሌላ በኩል በሰው ልጆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ የጾታ ክፍፍል መኖር የለበትም በማለት የሚሞግቱም ብዙ ናቸው።

ዜናውን የሰሙ ግብጾች ምንም ጉዳት በማያስከትል ተንቀሳቃሽ ምስል እንዴት እንድ ሰው ለእስር ሊዳረግ ይችላል በማለት በዜናው ተድነቀዋል።

በቅርቡ በሳውዲ ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ መፈቀዱን በመጥቀስ ይህ እስር አግባብ አለመሆኑን የሚከራከሩ ግብጻዊያን በርካቶች ናቸው።

''የሳውዲ አረቢያው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሰልማን አዲስ ሳውዲ አረቢያን ማየት አይፈልጉም? የሙዚቃ ድግሶችን፣ ሲኒማ ቤቶችን እና የባህር ዳርቻ መዝናኛዎችን በሳውዲ ማየት አይፈልጉም?'' በማለት አንድ ተዋቂ የግብጽ የቴሌዚዥን ፕሮግራም አቅራቢ ጠይቋል።

አል ሲሲ ግብፅ በአባይ ላይ ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ ቃል ገቡ