ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እና አሜሪካ ተፋጠዋል

የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት ጆን ቦልተን Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት ጆን ቦልተን ፍርድ ቤቱን «ሕጋዊነት የሌለው» ብለውታል።

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዜጎቼ ላይ ብይን የሚሰጥ ከሆነ ቅጣት አስተላልፋለሁ ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀች።

ፍርድ ቤቱ አፍጋኒስታን ውስጥ እሥረኞችን አሰይቃይተዋል ያላቸውን አሜሪካውያን ወታደሮችን ሊቀጣ መሆኑን ተከትሎ ነው አሜሪካ ማስጠንቀቂያ የሰነዘረችው።

የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ የሆኑት ጆን ቦልተን ፍርድ ቤቱን «ሕጋዊነት የሌለው» ካሉ በኋላ «አሜሪካ ዜጎቿን ለመከላከል የተፈለገውን ሁሉ ታደርጋለች» ሲሉ ተደምጠዋል።

አሜሪካ ዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ካልተቀላቀሉ ሃገራት መካከል አንዷ ነች።

አሜሪካ ፍልስጤምን አስጠነቀቀች

በ123 ሃገራት እውቅና አግኝቶ በአውሮፓውያኑ 2002 ላይ የተቋቋመው የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የዘር ማጥፋት እና የጦር ወንጀለኞችን ለመቅጣት ታስቦ የተዋቀረ ነው።

የአፍሪቃ ሃገራት ላይ አድልዎ ያሳያል ያሉ አንዳንድ የአህጉሪቱ ሃገራት ከፍርድ ቤቱ ራሳቸውን ለማግለል ሲዝቱ ይሰማሉ። ከአንድ ዓመት በፊት ቡሩንዲ ከፍርድ ቤቱ እራሷን በማግለል ቀዳሚ ሆናለች።

ጆን ቦልተን አፍጋኒስታንም ሆነች የፍርድ ቤቱ አባል የሆነ ሃገር ወታደሮቹ እንዲመረመሩ ሃሳብ ሳይሰጥ ፍርድ ቤቱ ይህን ማድረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ስሜት ያለው ንግግር አሰምተዋል።

ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ራሱን ችሎ መሰል እርምጃዎችን የመውሰድ ሥልጣን አለው።

የመደመር ጉዞ ወደ አሜሪካ

ፍርድ ቤቱ በውሳኔው የሚፀና ከሆነ አሜሪካ የፍርድ ቤቱ ዳኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እንዲሁም በአሜሪካ የሚገኝ ሃብት ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ትችላለች።

«ዳኞቹን በወንጀል ህጋችን እንከሳቸዋለን፤ ለፍርድ ቤቱ ድጋፍ የሚያደርግ ማንኛውም ድርጅትም ተመሳሳይ ዕጣ ይጠብቀዋል» ብለዋል አማካሪው።

ፍርድ ቤቱ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካን ዛቻ በፅኑ ተቃውሞታል።

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያን ንብረት ተዘረፈ