የማክሰኞ ምሽት አጫጭር ዜናዎች

አጭር የምስል መግለጫ የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን አስክሬን የመጨረሻ ስንብት በአክራ

ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር ላይ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከዛሬ ጀምሮ መልቀቅ እንደሚጀምሩ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ አስታወቁ።

ይህን ያሉት ከሃያ ዓመታት በኋላ ተዘግቶ የነበረው የሁለቱ አገራት ድንበር እንደገና መከፈቱን ተከትሎ ነው።

ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬ ግንባር

ጋና

የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ ኮፊ አናን አስክሬን ወደ ትውልድ አገራቸው ጋና ማረፉ ተገለፀ።

ወዳጆቻቸው አክራ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል በመገኘት አስክሬናቸውን እየተሰናበቱ ነው።

የዓለም መሪዎች፣ የንጉሳውያን ቤተሰቦች ሐሙስ በሚፈፀመው የቀብር ስነ ስርዓታቸው ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

'መቐለ' በምፅዋ

ዚምባብዌ

በዚምባብዌ የኮሌራ ወረርሽኝ አገርሽቶ 20 ሰዎች ሲሞቱ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች በጠና መታመማቸውን የአገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታወቁ።

በዋና ከተማዋ ሃራሬ የአደጋ ጊዜ የታወጀ ሲሆን ስጋና የአሳ ምርቶች በከተማ እንዳይሸጥ እግድ ተጥሏል።

የቆሻሻ መተላለፊያ ቱቦ ፈንድቶ የውሃ ብክለት ማስከተሉ እንደ ምክንያትነት ተጠቅሷል።

ስለ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጥቂቱ

ታንዛኒያ

ታንዛኒያ በሰው ሰራሽ ጥፍርና የአይን ሽፋሽፍት አጊጦ ወደ ፓርላማ መግባት አገደች።

እግዱ የተጣለው የጤና ጥበቃ ምክትል ሚንስትሩ ሰው ሰራሽ ጥፍርና የአይን ሽፋሽፍት ማድረግ በጤና ላይ አደጋ እንደሚያስከትል ከተናገሩ በኋላ ነው።

የፓርላማ አባላትን ብቻ ሳይሆን ለጉዳይ ወደ ፓርላማ የሚመጡትንም ይመለከታል ተብሏል።

በታንዛኒያ ፓርላማ ውስጥ አጭር ቀሚስና ጂንስ መልበስም የተከለከለ ነው።

ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት?

ሊቢያ

የተሳፈሩበት መርከብ ሰጥሞ ከአንድ መቶ በላይ ስደተኞች በሊቢያ ዳርቻ ላይ እንደሞቱ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን አስታወቀ።

በህይዎት የተረፉት 276 ስደተኞች ወደ ሊቢያ ወደብ ከተማ ከሆምስ መወሰዳቸው ተገልጿል።

በዚህ ዓመት ብቻ የሜድትራኒያንን ባህር ለማቋረጥ ሲሉ 1500 ስደተኞች ሕይዎታቸውን አጥተዋል።

ደቡብ አፍሪካ

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በየዕለቱ የሚገደሉ ሰዎች ቁጥር 57 መድረሱን የሃገሪቱ ፖሊስ ይፋ አደረገ።

የፖሊስ ሚኒስትር በሄኪ ቼሌ የግድያው መጠን በጦርነት ቀጠና ከሚያጋጥመው ጋር የተቀራረበ ነው ብለዋል።

ለግድያ ወንጀሎች መበራከት ከወሮበላ ቡድኖች ጋር የተያያዙ የበቀል ድርጊቶች፣ የቡድንና ፖለቲካዊ ግድያዎች እንደ ዋነኛ ምክንኣት ተጠቅሰዋል።

የተባበሩት መንግስታት

ባለፉት ሶስት ዓመታት በርሃብ የሚሰቃዩ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት በሪፖርቱ ገለፀ።

ለቁጥሩ ማሻቀብ የአየር ንብረት ለውጥ አንዱ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት

አሜሪካ

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዜጎቼ ላይ ብይን የሚሰጥ ከሆነ ቅጣት አስተላልፋለሁ ስትል አሜሪካ አስጠነቀቀች።

ፍርድ ቤቱ አፍጋኒስታን ውስጥ እሥረኞችን አሰይቃይተዋል ያላቸውን አሜሪካውያን ወታደሮችን ሊቀጣ መሆኑን ተከትሎ ነው አሜሪካ ማስጠንቀቂያ የሰነዘረችው።

አሜሪካ ዓለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ካልተቀላቀሉ ሃገራት መካከል አንዷ ነች።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ