በርካታ ስደተኞች ሊቢያ ባህር ዳርቻ ላይ ሰጥመው ሞቱ

ስደተኞች አንስተኛ ጀልባ ላይ ተጭነው Image copyright Reuters

በያዝነው የፈረንጆቹ ወር መጀመሪያ ላይ ከ100 መቶ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ሊቢያ የባህር ዳርቻ ላይ ሰጥመው መሞታቸውን አንድ የግብረ ሰናይ ደርጅት አስታወቀ።

የሜደስን ሳንስ ፍሮንቲርስ ሪፖርት እንደሚለው፤ ነሐሴ 26/2010 ዓ.ም ላይ ሁለት አንስተኛ ጀልባዎች ጉዟቸውን ጀመሩ። ይሁን እንጂ ከፕላስቲክ የተሰራችው አንደኛዋ ጀልባ ከግዑዝ ነገር ጋር ተጋጭታ አየር ጎድሏት ሰጥማለች።

ከአደጋው የተረፉ 276 የሚሆኑ ስደተኖች የሊቢያ የወደብ ከተማ ወደ ሆነችው ካሆምስ ተወስደዋል።

ተጎጂዎቹ ከመዲናዋ በደቡብ ምስራቅ በምትገኝው ካሆምስ ሆስፒታል ውስጥ የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ነው።

ካለሁበት 1፡ ''በሜዲትራንያን ባህር ከመስመጥ መትረፌ ሁሌም ይደንቀኛል"

የሜደስን ሳንስ ፍሮንቲርስ ሪፖርት እንደሚለው ከሆነ ስደተኞቹን ፖሊስ በዓይነ ቁራኛ እየተከታተላቸው ነው።

ከተጎጂዎቹ መካከል ነብሰ-ጡር እናቶች፣ ጨቅላዎች እና ህጻናት ይገኙበታል።

ሜደስን ሳንስ ፍሮንቲርስ የሳምባምች ታማሚዎችን እና በነዳጅ ፍሳሽ ምክንያት ቆዳቸው የተቃጠሉ ሰዎችን አክሚያለው ብሏል።

ባለፉት 9 ወራት ብቻ ከ1500 ስደተኞች በላይ ሜዲትራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ጥረት ሲያደርጉ ህይወታቸው ማለፉን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ገልጿል።