የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል፤ የጨዋታዎቹ ግምትም እንዲሁ

ሊቨርፑል ከቶተንሃም Image copyright Getty Images

አምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያ ሲቀጥል ሊቨርፑል ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ውጤት ገማቹ ማርክ ላውረንሰን እንዲህ ይላል።

ቅዳሜ

ቶተንሃም ከሊቨርፑል

ምንም እንኳ ሊቨርፑል ዌምብሌይ ላይ የነበረውን ጥላ ቢገፍም ይሄኛው ጨዋታ ቀላል ይሆናል ብዬ አላስብም ይላል ላውሮ።

ለዚህ ነው ፍልሚያው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ብዬ የማስበው ሲል ያክላል።

ሁለቱም ቡድኖች በጥሩ አቋም ላይ ናቸው፤ ውጤቱም የሚያስከፋቸው አይመስለኝም።

ግምት፡ 1 - 1

ቦርንማውዝ ሌይስተር

ቦርንማውዝ የዚህን ዓመት የመጀመሪያ ሽንፈታቸው ቀምሰዋል፤ በቼልሱ 2 ለምንም በመሸነፍ።

ለይስተርም እንዲሁ ያለፈው ጨዋታቻውን በሽንፈት ፈፅመዋል።

ቦርንማውዝ የማጥቃት ጨዋታን እንደሚመርጡ ባውቅም ሌይስተርም ለዚህ አያንስም የሚል እምነት አለኝ።

ግምት፡ 1 - 1

ቼልሲ ከካርዲፍ

እንደሊቨርፑልና ዋትፎርድ ሁሉ ቼልሲም እስካሁን ያደረጋቸውን ፍልሚያዎች በሙሉ ማሸነፍ ችሏል።

ካርዲፍ ደግሞ በተቃራኒው አንድም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻለም።

ካርዲፎች ቀላል ይሆናሉ ብዬ ባላስብም ቼልሲ እንደሚረታ ግን አልጠራጠርም።

ግምት፡ 3 - 0

አወዛጋቢው የእግር ኳስ ዳኞች ማስመሪያ

ሃደርስፊልድ ከክሪስታል ፓላስ

ለክሪስታል ፓላስ አንድ ያለው መልካም ዜና ዊልፍሬድ ዛሃ ከደረሰበት ጉዳት ማገገሙ ነው።

ፓላስ ያለ ዛሃ ጨዋታዎችን ለማሸነፍ እየከበደው የመጣ ይመስላል።

ሃደርስፊልድ እስካሁን አንድም ጨዋታ ማሸነፍ ካልቻሉ አምስት ቡድኖች መካከል ናቸው።

ግምት፡ 1 - 2

ማንቸስተር ሲቲ ከፉልሃም

ፉልሃም ከብራይተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ ሁለት ለዜሮ መምራት ቢችሉም የኋላ ኋላ ነጥብ ተጋርተዋል።

ከሲቲ ጋር የሚኖራቸው ፍልሚያ እንደሚከብዳቸው አልጠራጠርም።

ግምት፡ 3 - 0

ቢጫና ቀይ ካርዶች እንዴት ወደ እግር ኳስ ሜዳ መጡ?

ኒውካስል ከአርሴናል

የኒውካስትሉ አሠልጣኝ ራፋኤል ቤኒቴዝ የቡድኑ የመከላከል ስታይል ቢያስተቻቸውም ደጋፊዎቻቸው አሁንም ከእርሳቸው ጎን ናቸው።

በዚህ ጨዋታ እንደሚሳካላቸው አስባለሁ።

ቤኒቴዝ አምና በሜዳቸው አርሴናልን ማሸነፍ ችለዋል፤ ዘንድሮም ይደግሙታል ብዬ አስባለሁ።

ግምት፡ 2 - 1

ዋትፎርድ ከማንቸስተር ዩናይትድ

ዋትፎርደ አስገራሚ አቋም ላይ ናቸው። የዩናይትድ የመከላከል ብቃት የሚፈተነው አሁን ነው።

በርንልይን በጥሩ ሁኔታ ያሸነፉት ዩናይትዶች አሁንም ይደግሙታል የሚል ግምት አለኝ።

ግምት፡ 0 - 2

ዕሁድ

ዎልቭስ ከበርንሌይ

ዎልቭስ የመጀመሪያ ሶስት ነጥባቸውን ከዌስትሃም ማግኘት ችለዋል።

በርንሌይ ግን እስካሁን ሶስት ነጥብ እንደራቃቸው ይገኛል።

ግምት፡ 0 - 2

ኤቨርተን ከዌስትሃም

ዌስትሃም እስካሁን ምንም ነጠብ ማምጣት ያለቻለ ብቸኛው ቡድን ነው፤ አሰልጣኝ ማኑዌል ፔሌግሪኒም ቡድኑን ለማዋቀር ጥረታቸውን ቀጥለዋል።

በሌላ በኩል ኤቨርተን እስካሁን ሽንፈት አልቀመሱም፤ ይሄንንም ጨዋታ ከማሸነፍ ወደኋላ አይሉም ባይ ነኝ።

ግምት፡ 2 - 1

ሰኞ

ሳውዝሃምፕተን ከብራይተን

ሁለቱም ቡድኖች ከአራት ጨዋታ አራት አራት ነጠብ መሰብሰብ ችለዋል።

ይህኛውን ጨዋታ አቻ በመውጣት አንድ አንድ ነጠብ ያክላሉ የሚል እምነት አለኝ።

ግምት፡ 1 - 1

ተያያዥ ርዕሶች