የጋሬዝ ክሩክስ ቡድን ሃዛርድ፣ ዛሃ እና ሚልነር ተካተውበታል። ቀሪዎቹ ተጫዋቾችስ እነማን ናቸው?

David de Gea Image copyright PA

ቼልሲ እና ሊቨርፑል ሦስት ነጥብ በመሰብሰብ የማሸነፍ ጉዟቸውን ሲቀጥሉ ማንቸስተር ሲቲም አሸንፎ እየተከተላቸው ነው።

ማንቸስተር ዩናይትድ አስፈላጊ የሆነ ድሉን ዋትፎርድ ላይ ያስመዘገበ ሲሆን ሴንት ጀምስ ፓርክ ላይ አርሴናልም ሦስት ነጥቦችን ሰብስቧል።

እነማን በሳምንቱ ቡድን ውስጥ እንዲካተቱ የሚያስችላቸውን ብቃት አሳዩ?

ኬኒያዊው አትሌት የዓለምን የማራቶን ክብረ ወሰን ሰበረ

''ብሔርተኝነት'' እያጠላበት ያለው እግር ኳስ

ግብ ጠባቂ - ዴቪድ ደ ሂያ

ዴቪድ ደ ሂያ፡ ደ ሂያ ባለቀ ሰዓት ከክርስቲያን ካባሴል የተሞከረበተን ድንቅ ኳስ አድኗል።

ግብ ጠባቂው ከስፔን ጋር መጥፎ የሚባል ውድድር ያሳለፈ ቢሆንም ለማንቸስትር ዩናይትድ ነጥቦችን እያስገኘ ነው።

ይህን ያውቃሉ? በዋትፎርዱ ጨዋታ ጎል ላይ ከተሞከሩት አምስት ኳሶች አራቱን ዴቪድ ደ ሂያ አድኗል። ይህም ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ካዳናቸው ኳሶች ጋር እኩል ነው።

Image copyright Getty Images, Rex Features, Reuters

ተከላካዮች - ክሪስ ስሞሊንግ፣ ጆ ጎሜዝ እና ቨረጂል ቫን ዳይክ

ክሪስ ስሞሊንግ፡ ጆሴ ሞውሪንሆ ተከላካይ ክፍላቸው ችግር እንዳለበት የገለጹ ሲሆን አሁን ተጫዋቾቻቸው ይህን በመመለስ ላይ ይገኛሉ። ክሪስ ስሞሊንግ በአዲስ የጸጉር አቆራረጥ ከመምጣቱም በላይ በዋትፎርድ ጨዋታ ድንቅ ሆኖ አምሽቷል።

የጸጉር አቆራረጡ እና ድንቅ ጎሉ ተያያዥ ከሆኑ መልካም ዕድል ነው።

ይህን ያውቃሉ? ስሞሊንግ ግብ ባስቆጠረባቸው 11 ጨዋታዎች ላይ ቡድኑ አሸንፏል። ይህም ክብረወሰኑን ከሪያን ባብል ጋር እንዲጋራ አስችሎታል።

ጆ ጎሜዝ፡ ተጫዋቹ ከቶተንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ሁለተኛ አጋማሽ ሉካስ ሞውራን ያስቆመበት አካሄድ የቡድኑን ጉዞ ያቋረጠ ነበር።

ይህ ተጫዋች ላለፉት ዓመታት ካየኋቸው ድንቅ ተካላካዮች መካከል አንዱ መሆኑን ከሳምንታት በፊት ገልጬ ነበር። ወደፊት የእንግሊዝ አምበል ሊሆኑ ከሚችሉ ተጫማቾች መካከልም አንዱ ነው።

ይህን ያውቃሉ? ሦስት ኳሶችን ከማስጣሉ እና ከግብ አካባቢ ከማራቁም በላይ ዘጠኝ ጊዜ ኳሶችን ነጥቋል።

ቪርጂል ቫን ዳይክ፡ ሃሪ ኬን ምንም ኳስ አልሞከረም። ቨርጂል ቫን ዳይክ ግዙፍ ከመሆኑም በላይ ጠንካራ እና ከኳስ ጋር ያለው ችሎታ ድንቅ ነው። የእንግሊዙ አምበል ለዚህ የተዘጋጀ አይመስልም ነበር።

የቶተንሃም ተጫዋቾች ከተደበቁበት ጨዋታዎች አንዱ ይህ ሲሆን ቫን ዳይክ በበኩሉ ሜዳ ላይ የኦስካር አሽናፊ ተዋናይ ይመስል ነበር።

ይህን ያውቃሉ? ማንም ተጫዋች ዌምብሌይ ላይ የቫን ዳይክን ያህል ኳስ ከአደጋ ክልል አላራቀም።

Image copyright Rex Features/Getty Images/Reuters

አማካዮች - ማሩዋን ፌላይኒ፣ ጀምስ ሚልነር፣ ኤደን ሃዛርድ እና ሪያን ፍሬዘር

ማሩዋን ፌላይኒ፡ ማሩዋን ፌላይኒ በማንቸስትር ዩናይትድ ማሊያ በመድመቅ ላይ ይገኛል። ዴቪድ ሞዬስ ሲያስፈርሙት ብዙዎች ለቡድኑ የማይመጥን ሲሉ ገልጸውታል።

ከዋትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ የችግራቸው ሁሉ መፍትሄ ሆኖ ታይቷል። እንደዚሁ ከቀጠለ ፌላይኒ ለኤቨርተን የነበረውን ያህል በማንቸስተር ዩናይትድም አስፈላጊ ይሆናል።

ይህን ያውቃሉ? ፌላይኒ ከአስር የአየር ላይ ኳሶች ሰባቱን ለማግኝት ችሏል።

ጀምስ ሚልነር፡ ከ16 ዓመቱ ጀምሮ ድንቅ እግር ኳስን ሲጫወት ለነበረ ተጫዋች ከ16 ዓመታት በኋላም ይህንኑ መድገሙ የሚያስገርም አይደለም።

ሚልነር ጨዋታን የሚረዳበት መንገድ ከፍተኛ ሲሆን ከወዲሁ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች የመሆን ዕድል ካላቸው መካከል ነው። የግል ሽልማት ዋንጫ ካነሳ ቡድን ጋር መሆን እንዳለበት አምናለሁ።

ይህን ያውቃሉ? ጀምስ ሚልነር ከሞሃመድ ሳላህ እኩል ከፍተኛውን ዕድል ለቡድኑ ከፈጠሩ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።

ኤደን ሃዛርድ፡ የመጀመሪያው የኤደን ሃዛርድ ጎል ድንቅ ነበር።

ካርዲፍ ላይ ሦስት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለው ቤልጂየማዊ የህይወቱን ድንቅ የአግር ኳስ ጊዜ በማሳለፍ ላይ ነው።

ይህን ያውቃሉ? ለቼልሲ ከአንድ ጊዜ በላይ ሃትሪክ ካስቆጠሩ አራት ተጫዋቾች መካከል ኤደን ሃዛርድ አንዱ ነው።

ሪያን ፍሬዘር፡ ፍሬዘር በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ሳይነካ ባይወድቅ ኖሮ በአጨዋወቱ ከእኔ ከፍተኛ ሙገሳን ያገኝ ነበር። በጨዋታው ብዙ ገጠመኞች የነበሩ ቢሆንም ሳይነካ የወደቀበት ግን ከሁሉም የከፋው ነው።

የሳምንቱ ቡድኔ ውስጥ ቢካተትም በድጋሚ ያጤንኩት ጉዳይ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች አስመስለው መውደቅን አይወዱምና ነው።

ይህን ያውቃሉ? ሪያን ፍሬዘር በዚህ ጨዋታ በሦስት ጎሎች ላይ እጁ አለበት።

Image copyright Rex Features/Reuters

አጥቂዎች - ዊልፍሬድ ዛሃ፣ ማርኮ አርናውቶቪች እና ሮቤርቶ ፊርሚኖ

ዊልፍሬድ ዛሃ፡ ዛሃ ከጨዋታ በኋላ ቃለ መጠይቆች ላይ ስለሚደረጉብህ ጥፋቶች መናገርህን አቁም። ንክኪ ባለው ስፖርት ውስጥ ነው እየተሳተፈክ ነው ያለኸው። ደግሞ ጥሩ ተጫዋቾች ናቸው ጥፋት የሚፈጸምባቸው። ከዚህ ይልቅ በዚህ ዙሪያ ለምን አትሰራም?

ጆርጅ ቤስት ወይም ዮሃን ክራይፍ በተጫዋቾች ስለሚፈጸምባቸው ጥፋቶች ሲያማርሩ ሰምቼ አላውቅም።

ይህን ያውቃሉ? ካለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ ዛሃ በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ በአማካይ 1.5 ነጥቦችን ማግኘት ችሏል።

ማርኮ አርናውቶቪች፡ የኤቨርተኑ ጨዋታ የዌስትሃም ተጫዋቾች ከተረጋጉ እና መስመራቸውን ካገኙ በኋላ የሚኖራቸው ውጤት የሚያሳይ ነው።

አብዛኛው ነገር ደግሞ የተከናወነው በማርኮ አርናውቶቪች እና በአዲሱ የአጥቂ መስመር አጣማሪው አንድሬ ያርሞሌንኮ ነው።

ይህን ያውቃሉ? ከ2018 መጀመሪያ አንስቶ ሞሃመድ ሳላህ ብቻ ነው ከማርኮ አርናውቶቪች በላይ በጎሎች ላይ ተሳትፎ ያደረገው።

ሮቤርቶ ፊርሚኖ፡ ማንቸስተር ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ እንዳያሸንፍ ሊያደርገው የሚችለው ቡድን ሊቨርፑል ይመስላል።

ሆኖም በሊቨርፑል የአጥቂ መስመር ላይ አንድ ነገር ቢያጋጥም ኖሮ የተለየ ሁኔታ ይኖር ነበር።

ይህን ያውቃሉ? ሮቤርቶ ፊርሚኖ በአሰልጣኙ በየርገን ክሎፕ ስር በ61 የፕሪሚየር ሊግ ጎሎች ላይ በቀጥታ ተሳትፎ ነበረው።