ኢትዮጵያና ኤርትራ የመጨረሻውን የሠላም ስምምነት ፈረሙ

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ ንጉሥ ሳልማንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፣ ንጉሥ ሳልማንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች እሁድ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር ነው የተባለ የሰላም ስምምነት ጅዳ ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ተፈራረሙ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ስለተፈረመው ስለዚህ ስምምነት ዝርዝር ይዘት ይፋ የተደረገ ነገር እስካሁን ባይኖርም፤ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ስምምነቱን "ባለሰባት ነጥብ ስምምነት" ብቻ ሲል ገልጾታል።

"የጅዳው ስምምነት" ተብሎ ስለሚጠራው ስምምነት የሳኡዲ ባወጣው መግለጫ "ሁለቱ ሃገራት ሕዝብ መካከል ባለው የመልካምድር፣ የታሪክና የባህል የቅርብ ትስስር የሰላም ስምምነቱ በመንግስታቱ መካከል መደበኛ ግንኙነት እንዲፈጠር ያደርጋል" ብሏል።

ሞትና መፈናቀል በአዲስ አበባ ዙሪያ

'መቐለ' በምፅዋ

ኢትዮጵያና ኤርትራ፡ አዲስ ዓመትን በቡሬና በዛላምበሳ

ሁለቱ መሪዎች ስምምነቱን በቀይ ባሕሯ የወደብ ከተማ ጅዳ ላይ በተፈራረሙበት ወቅት የሳኡዲው ንጉሥ ሳልማን፣ አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሰልማን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ተገኝተዋል።

"በአፍሪካ ቀንድ ተስፋ የሚሰጥ ንፋስ እየነፈሰ ነው" ሲሉ ጉቴሬስ ከፊርማው ሥነ-ሥርዓት በኋላ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። "የሰላም ስምምነቱ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ብቻ የሚቆም ሳይሆን በኤርትራና በጂቡቲ መካከልም የሚፈፀም ይሆናል" ብለዋል።

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ንጉሥ ሳልማን ለኢትዮጵያና ለኤርትራ መሪዎች አብዱልአዚዝ አል ሳኡድ የተባለውን የሃገሪቱን ከፍተኛ ሜዳሊያ አበርክተውላቸዋል። መሪዎቹ ቀደም ሲልም ተመሳሳይ የክብር ሽልማት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተሰጥቷቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በሐምሌ ወር አሥመራ ላይ በተገናኙበት ወቅት ባለአምስት ነጥብ የሰላምና የወዳጅነት ባለአምስት ነጥብ ስምምነትን በመፈራረም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀውን ጠላትነታቸው እንዲያበቃ አድርገዋል።