አሜሪካዊቷ ደኒስ ኮርንክ ብስክሌት በማሽከርከር የዓለምን ክብረ ወሰን በእጇ አስገብታለች

ብስክሌተኛዋ ሙለር ደኒስ ኮርንክ በአሜሪካ፣ ኡታሃ በልምምድ ላይ እያለች Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ብስክሌተኛዋ ሙለር ደኒስ ኮርንክ

አሜሪካዊቷ ብስክሌት ጋላቢ በሰዓት ከ296 ኪሎ ሜትር በላይ በመሄድ በምድራችን ለብዙ ሰዎች የማይቻለውን 'እንደ ወፍ በመብረር' አስደምማለች።

ደኒስ ኮርንክ በዘርፉ ያስመዘገበችው ድል ብቸኛዋ አስብሏታል።

አሜሪካዊቷ ብስክሌተኛ በሰዓት 296.010 ኪሎ ሜትር በመጋለብ እልህ አስጨራሽ ውድድሯን ፈፅማለች።

የ45 ዓመት ጎልማሳዋ ብስክሌተኛ የራሷን ክብረ ወሰን ማሻሻል ብቻ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ በወንዶች ተይዞ የነበረውንም አሻሽላለች።

ብስክሌተኛዋ ደኒስ ኮርንክ "በሰዓት ወደ 300 ኪሎ ሜትር የሚጠጋን ርቀት መጓዝ የማይታመን ነው፤ ይሁን እንጂ የከፈልኩት መስዋዕትናትና ለብዙ ዓመታት ትኩረቴን በመስጠቴ፤ በዓለም ፈጣኗ ብስክሌተኛ እንድሆን አድርጎኛል" ትላለች።

በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች

ኦህዴድ አዲስ የፖለቲካ ፍልስፍና እከተላለሁ አለ

በቡራዩ ጥቃት ፈጻሚዎቹ የባንክ ሂሳብ ውስጥ 8 ሚሊዮን ብር ተገኘ፡ ዶ/ር ነገሪ

''ከ281 ኪሎ ሜትር በላይ መሄድ አይጠበቅብንም ነበር'' የምትለው ደኒስ ኮርንክ በ2016 በሰዓት 233 ኪሎ ሜትር በላይ በመጋለብ የሴቶችን ክብረ ወሰን ይዛ ነበር።

ነገር ግን በ1995 በሰዓት 268 ኪሎሜትር በመጋለብ በኔዘርላንዳዊው ፍሬድ ሮመፕለብረግ ተይዞ ወደ ነበረው ክብረ ወሰን አይኗ አረፈ።

ድሉን የራሷ ለማድረግ ህልሟ አደረገች፤ የውድድር መኪናዎችን በመከተል ልምምድ ማድረግ ጀመረች።

በዚህም ክብረ ወሰኑን የራሷ ማድረግ እንደሚቻል ተገነዘበች።

ይህች ብስክሌተኛ አንድ ቦይንግ አውሮፕላን በከፍታ ከመብረሩ አስቀድሞ ካለው ፍጥነት ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ተመስክሮላታል።

ያስመዘገበችውን ድል ተከትሎም በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ በሴቶችና በወንዶች በሚል ለየብቻ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አጠቃላ እንድትይዝ ጥሪዎች ቀርበውላታል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ