ኦህዴድ ስሙን ቀይሮ ኦዴፓ ተባለ

አዲሱ አርማ Image copyright OPDO Official FB

በጅማ ከተማ ድርጅታዊ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ስሙን ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) መቀየሩን ይፋ አድርጓል።

ከጥቂት ወራት ቀደም ብሎ ድርጅቱ መለያው የሆኑትን ስያሜውንና አርማውን ለመቀየር እየተዘጋጀ እንደነበር ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ዛሬ ስያሜውን ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ሲቀይር በተጨማሪም ከቀረቡት መለያ አርማዎች ውስጥ የተመረጠው ላይ ማሻሻያ በመድረግ እግዲቀርብ መወሰኑን ከድርጅቱ የወጣ መረጃ ያመለክታል።

ኦህዴድ አብዮታዊ ዴሞክራሲንና ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ታሪክ ሊያደርጋቸው ይሆን?

ኤርትራ በምሽት ድንበር ማቋረጥን ከለከለች

በተጨማሪም ፓርቲው ከመስራችና ነባር አባላቱ መካከል አቶ አባዱላ ገመዳ፣ አቶ ሱለይማን ደደፎ፣ ወ/ሮ ጊፍቲ አባሲያ፣ አቶ እሸቱ ደሴ፣አቶ ድሪባ ኩማ፣ አቶ ጌታቸው በዳኔ፣ አቶ ግርማ ብሩ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ አቶ ደግፌ ቡላ፣ አቶ አበራ ኃይሉ፣ አቶ ተፈሪ ጥያሩ፣ አቶ ኢተፋ ቶላ እና አቶ ዳኛቸው ሽፈራውን በክብር አሰናብቷል ተብሏል።