ጉግል ስለእርስዎ ብዙ ያውቃል፤ እርስዎስ ስለ ጉግል ምን ያውቃሉ? እነሆ 10 ነጥቦች

ጉግል ለሁለት ተማሪዎች የተሰጠ 'የቤት ሥራ' ነበር ቢባል ማን ያምናል? Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ጉግል ለሁለት ተማሪዎች የተሰጠ 'የቤት ሥራ' ነበር ቢባል ማን ያምናል?

ጉግል 20ኛ ዓመት የልደቱን በዓሉን ሊያከብር ሽር ጉድ እያለ ነው። ይህን ተንነተርሰን ስለ ጉግል ምናልባት የማያውቋቸው 10 ነጥቦች ይዘን ብቅ ብለናል።

ከጉግል በፊት ሕይወት ምን ትመስል ነበር? አንድ መረጃ በፍጥነት ሲፈልጉ ምን ያደርጉ እንደነበር ያስታውሱታል?

ምንም ይፈልጉ ምን፤ የአንድን ቃል ትርጓሜ እና አፃፃፍም ይሁን የቦታ ጥቆማ፤ ብቻ የሆነ ነገር ሲፈልጉ ወደ ጉግል መሮጥ የተለመደ ሆኗል። 'ዕድሜ ይስጠውና' ጉግል ፊት ነስቶን አያውቅም፤ 'ጎግለው' እንዲል የሃገሬ ሰው።

የደመራ በዓል ዝግጅትና አከባበር በምስል

«አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7

በየሰከንዱ ይላል ፎርብስ የተሰኘው መፅሄት መረጃ. . .በየሰከንዱ 40 ሺህ ሰዎች 'ይጎግላሉ'፤ በቀን 3.5 ቢሊዮን እንደማለት ነው።

ጉግል ሁሉ ነገር ሆኗል፤ ማስታወቂያ በሉት፣ የቢዝነስ ዕቅድ እንዲሁም ግላዊ መረጃ መሰብሰቢያ ነው።

እንግዲህ እውነታውን ልናፈራርጠውም አይደል፤ እናማ ስለጉግል አንድ ሚስጢር እንንገርዎት። መረጃ ፍለጋ ወደ ጉግል በሮጡ ቁጥር ጉግል ስለእርስዎ የተወሰነ መረጃ ይሰበስባል።

«ግን ምን ያህል መረጃ?» አሉን?፤ መልካም! እነሆ የጠየቁንን ጨምሮ ስለጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች።

፩. ስያሜው

Image copyright Getty Images

ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።

በእንግሊዝኛው 'googol' ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።

እና ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።

አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ

፪. የጀርባ ማሻ

Image copyright Getty Images

የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው 'Backrub' ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።

ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ።

ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።

. የተንጋደደ

አጭር የምስል መግለጫ አያስቦ፤ እይታዎ ሳይሆን ምስሉ ነው የተንጋደደው

ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።

እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።

ውጤቱ አዩት?

፬. ፍየሎች

Image copyright Getty Images

ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው።

አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ።

ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።

፭. እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ኢንስታግራም ወይ ቴሌግራም ይጠቀማሉ? የማን ንበረት እንደሆኑስ ያውቃሉ?

ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።

ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።

፮. ዱድል

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የጉግል የተማሪዎች ውድድር

ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።

ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።

አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።

ከደሴ - አሰብ የሞላ?

፯. ለሌሎች ያመለጠ ዕድል

በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።

ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።

አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።

፰. መሪ ቃላት

Image copyright Getty Images

'ከይሲ አይሁኑ' ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።

'ምን አገባው' የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።

፱. ምግብማ ግድ ነው

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከጉግል ዋና መሥሪያ ቤት የማይጠፋ ነገር ቢኖር ምግብ ነው

ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።

የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።

፲. የጉል ባልንጀራ

Image copyright Getty Images

የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።

ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።

አጀብ ነው!

«አዲስ አበባ የሁሉም ናት» አርበኞች ግንቦት 7

ተያያዥ ርዕሶች