በኢራን በቤት ውስጥ የተመረዘ መጠጥ የጠጡ 42 ኢራናውያን ሞቱ

Soldiers inspecting seized alcohol Image copyright Mehr

በኢራን የተመረዘ መጠጥ የጠጡ 41 ግለሰቦች መሞታቸውን የሐገሪቱ የመንግስት ቃል አቀባይ ተናገሩ።

የጤና ሚኒስትር ቃል አቀባይ የሆኑት ኢራጅ ሐሪርቺ እንዳሉት 16 ሰዎች የአይን ብርሃናቸውን ሲያጡ 170 ሰዎች ደግሞ ይህንን የተመረዘ መጠጥ ከጠጡ በኋላ ወደ ኩላሊት እጥበት ሄደዋል።

ባለፉት ሶስት ሳምንታት በአምስት አውራጃዎች የሚኖሩ 460 ሰዎች ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል የ19 ዓመት ሴት ትገኝበታለች።

ያልተጠበቁ ስሞች በአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ

በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት

ኢትዮጵያ 8.5 በመቶ ዕድገት ታሥመዘግባለች፡ አይ.ኤም.ኤፍ.

በኢራን የአልኮሆል መጠጦች ሕገወጥ ቢሆኑም በቤት ውስጥ ኢታኖል ተጨምሮበት የሚዘጋጅ መጠጥ ግን ተስፋፍቶ ይገኛል።

ይህ ኢታኖል ተደባልቆበት በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መጠጥ አደገኛ ሜታኖል ተቀላቅሎበትም ይዘጋጃል።

ፖሊስ በደቡባዊ ኢራን በምትገኘው የባንዳር አባስ ከተማ በቤት ውስጥ ይህንን መጠጥ የሚያዘጋጁ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ነበር።

ይሁን እንጂ አሜሪካ በኢራን ላይ ማዕቀብ ከጣለች በኋላ በተፈጠረ የዶላር እጥረት ምክንያት የአልኮል መጠጦችን የሚጠቀሙ ግለሰቦች ርካሽ እና በቤት ውስጥ ወደሚዘጋጁ ፊታቸውን ሳያዞሩ እንዳልቀሩ ይገመታል።

የኢራን ፀረ አደንዛዥ ዕፅ ባለስልጣናት በየዓመቱ 730 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ 80 ሚሊየን ሊትር አልኮሆል ወደ ኢራን በህገወጥ መልኩ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

ኢራን ከ1979ኙ እስላማዊ አብዮት ወዲህ አልኮሆልን የከለከለች ቢሆንም ሙስሊም ያልሆኑ የሀገሪቱ ዜጎች ለተለያየ ተግባር በቤታቸው አልኮሆል ማዘጋጀት እንዲችሉ ተፈቅዷል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ