በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ባለሙያዎች ጥቃት ደረሰባቸው

የጤና ባለሙያዎች የሟች አስክሬንን ሲያጓጉዙ Image copyright AFP

ኢቦላ ዳግም ባገረሸበት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ቫይረስ የምትሉት ሀሰት ነው ሲል በተቆጣ የአካባቢው ነዋሪ ጥቃት ደረሰባቸው።

በምስራቃዊው ኮንጎ ክፍል ከሁለት ወር በፊት ዳግም ባገረሸው ኢቦላ ከ100 የሚበልጡ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተማ ቡቶሞ ከቤኒ ቀጥላ የኢቦላ ቫይረስ ስርጭት የታየባት ከተማ ናት።

በኡጋንዳ ድንበር ቅርብ በሆነችውና የአሳ ምርት በሚቸበቸብባት ሌላኛዋ ትቾይማ ከተማም ኢቦላ መታየቱ ተሰምቷል።ይሁን እንጂ ቫይረሱን ለመግታት በጤና ባለሙያዎች የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ ጥቃቶች በአካባቢው ማህበረሰብ በመፈፀሙ ችግሩን አስጊ አድርጎታል።

ኢቦላ በኮንጎ እየተዛመተ ነው

በእርጥብ ሳርና ቅጠል ጥቃትን ያስቆሙ አባቶች

የኢቦላ ቫይረስ ከሞቱት ሰዎች ጋር በሚደረግ ንክክኪ ይተላለፋል፤ በመሆኑም የሞቱትን ሰዎች በጥንቃቄና ለንክኪ በማያጋልጥ ቦታ መቅበር የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከሚደረግ ጥንቃቄ አንዱ ነው።

ይሁን እንጂ የሟች ቤተሰቦችና የአካባቢው ማህበረሰብ ይህንን እውነታ ለመቀበል ይቸገራሉ። በተለይ ደግሞ የሟች ግብዓተ መሬት ከመፈፀሙ አስቀድሞ ለስንብት የሟችን አስክሬን የሚነኩበት ልማድ ባለበት አካባቢ ጉዳዩን ፈታኝ አድርጎታል።

በዚህም ሳቢያ አራት የቀይ መስቀል የጤና ባለሙያዎች ሕይዎታቸው ያለፉ ሰዎችን ለቀብር ስነ ስርዓት በማጓጓዝ ላይ ሳሉ ቡቴሞ በተባለ አካባቢ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች መኪናቸው ላይ ድንጋይ በመወርወር በፈፀሙባቸው ጥቃት ሁለት የጤና ባለሙያዎች ለከፋ ጉዳት ተዳርገዋል።

«የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኢቦላ ላይ ትኩረት ባደረገውና በአሜሪካ ኒዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ምክርቤት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር በአገሪቱ ኢቦላ ያገረሸባቸውን አካባቢዎች ማንጊና እንዲሁም በቅርቡ ቫይረሱ የተከሰተባትን ቤኒን እንደጎበኙ ተናግረዋል።

"ከቀድሞው በባሰ በጣም አሳስቦኛል፤ አሁንም ጉዳዩ እንዳስጨነቀኝ ነው" ሲሉ የሁኔታውን ፈታኝነት በንግግራቸው ገልፀዋል።

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የተናገሩት ዳይሬክተሩ በአጠቃላይ 161 የተረጋገጠና የተጠረጠሩ ታማሚዎች፣ 106 የሚሆን ሞት ሲመዘገብ በሕይወት የተረፉ 45 ሰዎች እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

ማንኛውም እንቅስቃሴ በአገሪቱ መንግስት የሚመራና መንግስትም ጉዳዩን እየተከታተለ በማሳወቅ የተቻለውን እያደረገ እንደሆነ አስረድተው የዓለም ጤና ድርጅትም 200 የሚሆኑ የህክምና ባለሙያዎችን በሁለት ማዕከላት አሰማርቷል ብለዋል።

13, 700 የሚሆኑ ሰዎችም ክትባቱን ወስደዋል።

አቶ ጌታቸው አሰፋ የሀዋሳውን ጉባኤ ይታደማሉ?

ነገር ግን ቦታዎቹ ገጠራማና ከከተማ የወጡ በመሆናቸው በተለይ የደህንነት ጉዳይ አሳሳቢ ነው ፤ የጤና ባለሙያዎቹ በታጠቁ ሰዎችና በተለያዩ ቡድኖች ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በብኒ ከተማ 21 ሰዎች በሞቱበት የቦምብ ጥቃት ሳቢያ አገልግሎት የሚሰጡበትን ማዕከል ለቀናቶች ለመዝጋት ተገደዋል።

የአካባቢው ሰዎች በእነርሱ ላይ እምነት አለመጣላቸውም ሌላኛው ተግዳሮት እንደሆነ ገልፀው የገንዘብ ድጋፉም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስምረዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ