ሮናልዶ "ደፍሮኛል" ያለችው ሴት ከመብት ተሟጋቾች ከጎንሽ ነን የሚል ድጋፍ አገኘች

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለጁቬንቱስ በመጫወት ላይ ይገኛል Image copyright Reuters

ወይዘሪት ማዮርጋና ሮናልዶ በ2009 በላስቬጋስ ፓልም ሆቴልና ቁማር ቤት በሚገኘው ሬይን የምሽት ጭፈራ ቤት ይገናኛሉ። ከዚያም ጨዋታ ሲደራ ሮናልዶ ወደ ራሱ ማደሪያ እንደወሰዳትና እንደደፈራት ተናገራለች።

ፓርቹጋላዊው ሮናልዶ ይህ ዜና መጀመሪያ በጀርመን ጋዜጣ ላይ ሲወጣ "ሐሰተኛ ዜና" ነው በማለት አጣጥሎት ነበር

አሁን ክሱ በድጋሚ ከተንቀሳቀሰ በኋላም በቲውተር ገፁ ላይ ወ/ት ማዮርጋን በላስቬጋስ ሆቴል ደፈረኝ ማለቷን "በጭራሽ አላደረኩትም" ሲል ክዷል።

የፍስሀ ተገኝ የቤተሰብ ፍለጋ ጉዞ

ሞርጋን ፍሪማን በፆታዊ ትንኮሳ ለቀረበባቸው ውንጀላ ይቅርታ ጠየቁ

የኒውዮርኩ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ፈፀሙት በተባለ ጥቃት ሥራ ለቀቁ

የ33 ዓመቱ የጁቬንቱስ ተጫዋች " ማንኛውንም እና ሁሉንም ምርመራ" ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኑን ለዚህም ራሱን ማዘጋጀቱን ተናግሯል።

ወይዘሪት ማዮርጋ ይህ ድርጊት ከደረሰባት በኋላ ለላስ ቬጋስ ፖሊስ ማመልከቻ አስገብታ ነበር። ነገር ግን በሚቀጥለው ዓመት ክሷን እንድታቋርጥ እና ጉዳዩን ወደ ህዝብ እንዳታደርስ ተስማምተው የ375 ሺህ ዶላር ክፍያም ተስማምተው ነበር።

አሁን ግን ጠበቃዋ ይህ ስምምነት የተሰረዘ መሆኑን አሳውቀዋል።

ወይዘሪት ማዮርጋን ጠበቃዋ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት አልተገኘችም። የመገናኛ ብዙሃንን ውክቢያ በመሸሽ ከላስቬጋስ ሄዳለች።

"የእኔም እንቅስቃሴ አስተባባሪዎችና ሌሎች ወሲባዊ ትንኮሳና ጥቃትን ያጋለጡ ሴቶች ለካትሪን ማበረታቻ ድጋፋቸውን ሰጥተዋታል" ብለዋል ሌስሊ ስቶቫል።

ጠበቃዋ አክለውም " አሁን ካለችበት የስሜት ደረጃ በመነሳት ለመገናኛ ብዙሃን ምንም አይነት ቃለመጠይቅ ላለመስጠትና ራሷን በግልፅ ለህዝብ ላለማቅረብ ወስናለች" ብለዋል።

Image copyright Reuters

እንደጠበቃዋ ከሆነ ምንም እንኳ ጥቃቱ አስር ዓመት ሊሆነው ቢሆንም ደንበኛቸው ደረሰብኝ ካለችው ጥቃት በኋላ ከፍተኛ የሆነ ድብርት፣ ራስን የማጥፋት ሙከራ ውስጥ ማለፏን ተናግረዋል።

ለዚህም የስነልቦና ድጋፍ የሚሰጡ ባለሙያዎችን ማየቷን ጨምረው አስረድተዋል።

ሮናልዶ ለዚህ ክስ በ20 ቀን ውስጥ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል።

አሲድን እንደ መሳሪያ

የተነጠቀ ልጅነት

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ወሲባዊ ጥቃት አላደረስኩም አሉ

የላስ ቬጋስ ፖሊስም በ2009 ሰኔ ወር ይህንን ክስ ማጣራት ጀምረው እንደነበር አስረድተው በጉዳዩ ላይ ግን ተጠርጣሪ እንዳልነበራቸው አስረድተዋል።

"ከመስከረም 2018 ጀምሮ ግን ጉዳዩ እንደገና መታየት የጀመረ ሲሆን መርማሪዎቻችን በሚያገኙት መረጃ መሰረት ይከታተሉታል" ሲሉ ተናግረዋል።

የሮናልዶ ጠበቆች ከዚህ በፊት የጀርመኑን መፅሔት ፍርድ ቤት እንገትረዋለን ብለው ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ