እንግሊዝ "ራስን የማጥፋት" ተከላካይ ሚኒስትር ሾመች

በዓመት 4500 ዜጎች ራሳቸውን ያጠፋሉ Image copyright Getty Images

እንግሊዝ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን ነፍስን በገዛ እጅ የማጥፋት ጉዳይ ለመቀነስ በሚኒስትር ደረጃ ራስን የማጥፋት ተከላካይ ሚኒስትር (suicide prevention Minister) መሾሟ ተሰምቷል። ይህ ሹመት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ለነበሩት ጃኪ ፕራይስ ነው የተሰጠው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ይህን ሹመት የሰጡት የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በተከበረበት በትናንትናው ዕለት ነው።

የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ትናንት በለንደን ከ50 አገራት የመጡ የጤና ሚኒስትሮች በተገኙበት ተከብሮ ውሏል።

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ- ትህዴን ማን ነው?

“ትጥቅ መፍታት ለድርድር አይቀርብም”፡ መንግሥት

ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች

የእኚህ ሚኒስትር ተደራቢ ሥራ የሚሆነው በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን ነፍስን በገዛ እጅ የሚያጠፉ ዜጎችን ቁጥር የሚቀንስበትን መንገድ መሻት ይሆናል።

እንግሊዝ ውስጥ በተደረገ አንድ ጥናት የአእምሮ ጤና ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች በዘርፉ የሰለጠነን ሐኪም ለመጎብኘት እስከ ሦስት ወራት ለመጠበቅ ይገደዳሉ። ከነዚህም ውስጥ በአልኮል ሶስ የተጠመዱና በሐሴት-ሐዘን የስሜት መዋዠቅ (ባይፖላር ዲስኦርደር) ደዌ የተጠቁ ይገኙበታል።

በርካታ ዜጎችም ራስን ለማጥፋት እንደ አንድ ምልክት በሚታዩት የድብርትና ጭንቀት በሽታዎች ይሰቃያሉ።

አሁን አሁን መጠነኛ መቀነስ ታይቷል ቢባልም በእንግሊዝ በዓመት በአማካይ 4500 ዜጎች ነፍሳቸውን በገዛ እጃቸው ያጠፋሉ።