ሴራሊዮን በቻይና ብድር አየር ማረፊያ አልገነባም አለች

የቀድሞ ሴራ ሊዮን ፕሬዚዳንት ኤርነስት ባኢ ኮሮማ እና የቻይና ፕሬዚዳንት ዚ ጂንፒንግ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የቀድሞ ሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ኤርነስት ባኢ ኮሮማ እና የቻይና ፕሬዚዳንት ዚ ጂንፒንግ

አፍሪካዊቷ ሃገር ሴራሊዮን በብድር መልክ ቻይና እንድትገነባላት ተስማምታ የነበረውን የአየር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሰረዘች።

400 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ ይደረግበታል ተብሎ የነበረውን ይህንን ፕሮጀክት ስምምነቱን ተፈራርመው የነበሩት ከወራት በፊት በምርጫ ተሸንፈው ከሥልጣን የወረዱት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኤርነስት ባኢ ኮሮማ ነበሩ።

በወቅቱ የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሃገሪቱን ልትወጣው የማትችለውን ዕዳ ይቆልልባታል ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።

የሴራሊዮን ውሳኔ የተሰማው የአፍሪካ ሃገራት ለቻይና መክፈል ያለባቸው የዕዳ መጠን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል የሚሉ ሪፖርቶች እየተሰሙ ባሉበት ወቅት ነው።

የሃገሪቱ የአቪዬሽን ሚንስትሩ ካቢኔህ ካሎን ለቢቢሲ ሲናገሩ ሴራሊዮን በአሁኑ ሰዓት አዲስ አየር ማረፊያ ሳይሆን የሚያስፈልጋት ያላትን አየር ማረፊያ ማደስ ነው።

አፍሪካዊያን ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትን መጎብኘት ለምን ይከብዳቸዋል?

"ካሜራ ፊት ስቀመጥ ዘርም፣ ዘመድም ፓርቲም የለኝም " ቤተልሔም ታፈሰ

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ- ትህዴን ማን ነው?

ሴራሊዮን ከመዲናዋ ፍሪታዎን አቅራቢያ የሚገኝ አንድ አየር ማረፊያ ብቻ ነው ያላት። ከአየር ማረፊው ወደ ዋና ከተማዋ ዘልቀው መግባት የሚፈልጉ ተጓዦች ሄሊኮፕተር አልያም ጀልባ መጠቀም ግድ ይላቸዋል። የአቪዬሽን ሚኒስትሩ ጨምረው ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቀጣዩ እቅዳቸው ከአየር ማረፊያው ወደ መዲናዋ የሚያስገባ ድልድይ መገንባት ነው።

በሴራሊዮን የቻይና አምባሳደር የሆኑት ዉ ፔንግ ለቢቢሲ ሲናገሩ የአየር ማረፊያ ግንባታ ስምምነት መሰረዙ በሁለቱ ሃገራት መካከል የሚፈጥረው ቁርሾ የለም ብለዋል።

ከዓለም ባንክ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ እንዲሁም ጂ8 ተብለው የሚጠሩ እጅግ የበለጸጉ ሃገራት በድምሩ ለአፍሪካ ከሚሰጡት ብድር ሁሉ የቻይና የፍይናንስ አቅርቦታ ይበልጣል።

የቻይናን አካሄድ የማይወዱ የዘርፉ ባለሙያዎች ቻይና ሆን ብላ የአፍሪካ ሃገራትን የብድር ማነቆ ውስጥ እየከተተች ነው ይላሉ።

ቻይና ይህን አስተያየት አትቀበለውም።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ