በኢትዮጵያ እናቶችን የሚያገለግል 'ሁሉ በጤና' የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

በተለያየ ቋንቋ የተዘጋጀው መተግበሪያ Image copyright Dr. Amir Aman FB

እናቶችን የሚያገለግል 'ሁሉ በጤና' የተሰኘ መተግበሪያ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ይፋ ተደርጓል።

ስለ እናቶችና ህፃናት ጤና በአጠቃላይ ቤተሰብ ሊያውቋቸው ስለሚገቡ መረጃዎችን ከዚህ ቀደም የቤተሰብ ጤና መምሪያ ተብሎ በፅሁፍ ይሰራጭ ነበር።

ይሁን እንጂ ማንበብ የማይችሉና ያልተማሩ ቤተሰቦችን መድረስ ባለመቻሉ መተግበሪያው መሰራቱን ተመራጭ እንዳደረገው በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶችና ህፃናት ጤና ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃም ታሪኩ ይናገራሉ።

የዓለምፀሐይ፣ የፍስሃ እና የካሳሁን አዲስ ተስፋ

ስለ አንጀታችን የማያውቋቸው ስድስት አስገራሚ እውነታዎች

በመሆኑም ማንበብ ለማይችሉት መተግበሪያውን ስልካቸው ላይ በመጫን በቅድመ ወሊድ፣ በወሊድ ወቅትና ከወሊድ በኋላ፣ በህፃናት ክትባት ጊዜ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የእናቶችና ህፃናት ጤናን የተመለከቱ መረጃዎችን በድምፅ ማግኘት እንዲችሉ ያስችላቸዋል።

መተግበሪያው በአማርኛ ትግርኛና ኦሮምኛ የሚሰራ ሲሆን ለመጀመር ያህል በአማርኛ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

የእናቶች ጤና ዘርፈ ብዙ በመሆኑ መተግበሪያው ምን ያህል ምሉዕ ነው ያልናቸው ዳሬይክተሩ ከቤተሰብ ጤና መመሪያ ውስጥ የተወሰዱ ዋና ዋና መረጃዎች ወደ መተግበሪያው የተቀየሩ እንደሆኑ ይናገራሉ። መተግበሪያውንም ማንም ሰው በቀላሉ መጠቀም እንዲችል የሚያስችል ነው ብለዋል።

ምንም ዓይነት የኢንተርኔት አገልግሎት የማያስፈልገው ሲሆን በመተግበሪያው ላይ የተፃፈ ማውጫን በመጠቀም የሚፈልጉትን መረጃ በመምረጥ ማንበብም ሆነ በድምፅ መስማት የሚያስችላቸው ነው።

ምን ያህል እናቶችን መድረስ አንደሚቻል ያነሳንላቸው ዳይሬክተሩ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦች የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ መሆናቸውን፤ ከ60 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች በመኖራቸው መተግበሪያው ተመራጭ እንዲሆንና የተሻለ ተደራሽ መንገድ ሞባይል ነው ከሚል ውሳኔ ላይ እንደደረሱ ከኢትዮ ቴሌኮም ያገኙትን መረጃ በመጥቀስ ተናግረዋል።

«የምታገለው ለማንም ብሔር የበላይነት አይደለም» አቶ በቀለ ገርባ

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት በተባበሩት መንግሥታት ተሸለመ

በአብዛኛው የገጠር ቤተሰብ ውስጥ ስልክ የመጠቀም አዝማሚያው የወንዶች ቢሆንም መረጃውን ለትዳር አጋራቸውና ለልጆቻቸው ያጋራሉ ተብሎ ታሳቢ እንደተደረገም ይገልፃሉ።

ቢሆንም ግን ከሁለት ዓመት በፊት ያለው መረጃ እንደሚያሳየው 27 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይጠቀማሉ በዚህም እነርሱንም ተደራሽ ማድረግ እንደሚቻል ያስረዳሉ።

መተግበሪያው በማንኛውም ስልክ ላይ መጫን እንዲቻል ተደርጎ የተሰራ ሲሆን በተለይ በይበልጥ በዋጋም ቅናሽ ያላቸውና ቀላል ስልኮች ላይ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሰራ ነው። በሌሎችም ዘመናዊ ስልኮች ላይ መጫን ይቻላል።

ዳሬክተሩ የመተግበሪያው ስርጭት በቀጣይ የሚሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

የባለፈው ዓመት የሥነ-ህዝብና ጤና ጥናት እንደገለፀው ከ100 ሺህ እናቶች 412 በወሊድ ወቅት ይሞታሉ፤ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ጨቅላ ህፃናት ደግሞ ከ1000 ህፃነት 68ቱ ይሞታሉ።

ተያያዥ ርዕሶች