188 ሰዎችን አሳፍሮ የተነሳው የኢንዶኔዢያ ላየን ኤይር ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተከሰከሰ

188 ሰዎችን አሳፍሮ የተነሳው የኢንዶኔዢያ አውሮፕላን ተከሰከሰ

የፎቶው ባለመብት, AFP

188 ሰዎችን የተነሳው ላየን ኤይር ቦይንግ 737 የተሰኘ የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከዋና ከተማዋ ጃካርታ መብረር ከመጀመሩ ጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መከስሰከሱ ተሰምቷል።

ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ የተሰማው ጄቲ-610 በሚል መጠሪያ የሚታወቀው አውሮፕላን ባንግካ ቤሊቱንግ ወደተሰኘች ደሴት በመብረር ላይ ነበር።

ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ስለመኖራቸው እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።

እሁድ ሌሊት 7፡30 ገደማ መጓዝ የጀመረው ጄቲ-610 ዘመናዊ አውሮፕላን ከአንድ ሰዓት በረራ በኋላ መዳረሻው ይደርስ ነበር።

ከአደጋው በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ባልሠልጣናት፤ 178 ጎልማሶች፣ 1 ጨቅላ፣ ሁለት ህፃናት እና አብራሪዎችን ጨምሮ 7 የአየር መንገዱ ሰራቶኞች የአደጋው ሰለባ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ጠቁመዋል።

የሃገሪቱ አደጋ መቆጣጠር ባለሥልጣን ሱቶፖ ፑርዎ የአደጋውን ክብደት የሚያሳዩ ምስሎች በትዊተር ገፃቸው አጋርተዋል።

አውሮፕላኑ ባህር ላይ መውደቁ ደግሞ የተረፉ ሰዎች ሊኖሩ አይችሉም የሚለውን መላምት የጎላ አድርጎታል።

ከፈረንጆቹ 2016 ጅምሮ ጥቅም ላይ መዋል የጀመረው ቦይንግ 737 ሞዴል ወደገበያው ከገባ ጀምሮ እክሎች ያጋጥሙት እንደነበርም ተዘግቧል።

የኢንዶኔዢያው ላየን አየር መንገድ ወርሃ ነሃሴ ላይ ነበር ይህንን አውሮፕላን ገዝቶ የግሉ ያደረገው።

የደሴቶች ስብስብ የሆነችው ኢንዶኔዢያ በውሃ ከመከበቧ አንፃር የበረራ ትራንስፖርት ላይ ጥገኛ የሆነች ሃገር ናት፤ ቢሆንም አየር መንገዷ አደጋ አያጣውም።

2013 ላይ ደግሞ አንድ አውሮፕላኗ በእክል ምክንያት ውሃ ላይ ለማረፍ ቢገደድም 108 ተሳፋሪዎቹ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ ሳይደርስ መትረፍ ችለዋል።

በ2004 ዓ.ም በአውሮፕላን አደጋ ምክንያት 25 ሰዎች መሞታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,

እንኳን ወደ አውሮፕላን ካፌ በደህና መጡ