በታይላንድ ዋሻ ለሁለት ሳምንታት ጠፍተው የነበሩት ልጆች የማንችስተር ዩናይትድን ጨዋታ ተመለከቱ

ዋይልድ ቦይርስ ተብለው የሚታወቁት የህፃናት ወንዶች የእግር ኳስ ቡድን

የፎቶው ባለመብት, AFP

ለሁለት ሳምንት ያህል በታይላንድ ዋሻ ውስጥ ተቀብረው የነበሩት የህፃናት ወንዶች የእግር ኳስ ቡድን ህልማቸው የሆነውን የማንችስተር ዩናይትድን ጨዋታ ኦልድ ትራፎርድ ስታድየም ተገኝተው በትናንትናው ዕለት ተመልክተዋል።

ጠፍተው የነበሩት ልጆችና አሰልጣኛቸው በሐምሌ ወር የአለምን ዕይታ መሳብ ችለው ነበር።

ተአምራዊ በሆነ መንገድ ከዋሻው ከወጡ በኋላም ይህንን ጨዋታ እንዲያዩ ተጋብዘዋል።

ነገር ግን ደስታቸው ሙሉ ሊሆን አልቻለም፤ ታይላንዳዊው የሌስተር የእግር ኳስ ቡድን ባለቤት መሞት ዝግጅቱን ደብዘዝ አድርጎት ነበር።

ቪቺ ሲርቫድሀናፕራብሀና ሁለት ሰራተኞቹ፣ ፓይለቱና አንድ መንገደኛ ሄሊኮፕተሩ ከስታድየም ውጭ በመከስከሱ ሁሉም ሞተዋል።