ከኢትዮጵያና ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ስለተዘረፉ ቅርሶች ምን እናውቃለን?

ስለተዘረፉ የአፍሪካ ቅርሶች ምን ያውቃሉ?

ጥያቄ 1/6
ሃገር: ግብጽ

ሮሴታ ስቶን የግብጽን ጥንታዊ ጽሁፍ ለመረዳት ዋነኛ ቁልፍ ነው። በብሪታኒያ ሙዚየም ውስጥ የሚገኘውን 750 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ዝርግ ድንጋይ በ1799 ያገኘው ማነው?

 • 1. ግብጻዊ አሳ አስጋሪ
 • 2. የብሪታኒያ አርኪዮሎጂስቶች
 • 3. ፈረንሳያዊ የናፖሊዮን ወታደሮች

ትክክለኛ መልስ

በስፋት ተቀባይነት ያገኘው ታሪክ የፈረንሳይ ወታደሮች በአባይ ወንዝ ዳርቻ ምሽግ ሲቆፍሩ ድንጋዩን እንዳገኙ የሚያወሳው ነው።

ይህ የሮሴታ ድንጋይ ከሁለት ዓመት በፊት ለንደን ውስጥ በሚገኝ ሙዚየም ለህዝብ እይታ ቀርቦ ነበር።

ጥያቄ 2/6
ሃገር: ኢትዮጵያ

በ1868 የብሪታኒያ ወታደሮች ከመቅደላ ውጊያ በኋላ ከኢትዮጵያ ቅርሶችን ዘርፈዋል። ቅርሶቹን ለመውሰድ ስንት ዝሆኖችን ተጠቀሙ?

 • 1. 0
 • 2. 15
 • 3. 3

ትክክለኛ መልስ

ከመቅደላ የተዘረፉትን ቅርሶች ለማጓጓዝ 15 ዝሆኖችና 200 በቅሎዎችን ተጠቅመዋል። የሃይኖት መጻህፍት፣ የወርቅ ዘውድና ጽዋዎች ተዘርፈዋል።

በ1740 ገደማ ኢትዮጵያ ውስጥ ከወርቅና ውድ ከሆኑ ማዕድኖች የተሰራው ዘውድ በማዕከላዊ ለንደን በሚገኘው የቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየም ውስጥ ባለፈው ሚያዚያ ለእይታ ቀርቦ ነበር።

ጥያቄ 3/6
ሃገር: ኬንያ

ሰው በላዎቹ ፃቮ የሚባሉት እነማን ናቸው?

 • 1. ሙሰኛ የኬንያ ባለስልጣናት
 • 2. ከአንድ በላይ ባል ያላቸው ሴቶች
 • 3. ሰዎችን የሚበሉ ሁለት አንበሶች

ትክክለኛ መልስ

በ1899 በብሪታኒያ ወታደሮች ከመገደላቸው በፊት ከሞምባሳ እስከ ቪክቶሪያ ሃይቅ የሚደርሰው የባቡር መስመር በሚገነባበት ጊዜ ፃቮ በሚባል ቦታ 140 ሰራተኞችን የበሉ ሁለት አንበሶች ናቸው።

አንበሶቹ እንዲደርቁ ተደርገው አሁን አሜሪካ ቺካጎ ውስጥ ይገኛሉ

ጥያቄ 4/6
ሃገር: ዚምባብዌ

ከድንጋይ የተቀረጸችው የዚምባብዌ ወፍ የሃገሪቱ መለያ አርማ ናት። ቅርሶቹ በቅኝ ገዢዎች ከተዘረፉ በኋላ ከስምንቱ ጥንታዊ የድንጋይ ቅርጾች ስንቶቹ ወደ ዚምባብዌ ተመለሱ?

 • 1. 7
 • 2. 0
 • 3. 1

ትክክለኛ መልስ

ሰባቱ የድንጋይ ቅርጾች ዚምባብዌ ውስጥ ይገኛሉ። ከ15 ዓመታት በፊት ጀርመን በእጇ ያሉትን የመለሰች ሲሆን ስምንት የሚሆኑት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ውስጥ ይገኛሉ።

ጥያቄ 5/6
ሃገር: ካሜሩን

የባንግዋ ንግሥት በመባል የምትታወቀው የእንጨት ቅርጽ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ከካሜሩን የተወሰደች ናት። ሃገሬው የሴት ገጽ ያላትን ቅርጽ "ጁዊንዴም" ይላታል። ስያሜው ምን ማለት ነው?

 • 1. የእግዜር ሴት
 • 2. ታላቋ ጦረኛ
 • 3. ደስተኛ እናት

ትክክለኛ መልስ

በባንግዋ ህዝብ ቋንቋ "ጁዊንዴም" "የእግዜር ሴት" ማለት ነው። ይህ ቅርስ በ1899 እንዴት ጀርመናዊው የቅኝ ግዛት መልዕክተኛ እጅ ውስጥ እንደገባ እስካሁን አልታወቀም።

የባንግዋ ንግሥት ቅርጽ በአሁኑ ጊዜ ዳፐር በሚባል ተቋም ባለቤትነት ስር ፈረንሳይ ውስጥ ይገኛል።

ጥያቄ 6/6
ሃገር: ቤኒን

የቤኒን የነሃስ ቅርሶች ከምንድን ነው የተሰሩት?

 • 1. ከብራስ
 • 2. ከድንጋይ
 • 3. ከነሃስ

ትክክለኛ መልስ

በ1897 በብሪታኒያ ወታደሮች የተዘረፉት የቤኒን ብሮንዝ የተሰሩት ከብራስ ነው። ብዙዎቹ በእንግሊዝ፣ ጀርመንና አሜሪካ ውስጥ ይገኛሉ።

ከቤኒን መዳቦች ስር ያለ የብራስ ቅርስ

የበለጠ ይወቁ

በቅኝ ግዛት ወቅት በምዕራባዊያን ሃገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ቅርሶች ከአፍሪካ ተዘርፈዋል። ናይጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 2021 ሙዚየም ለመገንባት ማቀዷን ተከትሎ በጣም አስገራሚ በሆነ ሁኔታ የአውሮፓ ታላላቅ ሙዚየሞች ዋና ዋና ቅርሶችን በውሰት ሊሰጧት ተስማምተዋል።

የመቅደላ ቅርሶች

የፎቶው ባለመብት, AFP / Daniel LEAL-OLIVAS

የመቅደላ ቅርሶች የ18ኛው ክፍለ ዘመን የወርቅ አክሊል እና የንጉሣዊያን የሠርግ ልብስን ያካትታል። ከ185 ዓመታት በፊት በአውሮፓዊያኑ 1868 ከኢትዮጵያ (አቢሲኒያ) በብሪታንያ ወታደሮች አማካይነት የተወሰዱ ናቸው።

የቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዚየም የዘውድ አክሊል፤ ብር እና መዳብን ጨምሮ በተለያዩ ጌጦች የተሠራ ነው። አክሊሉ እና ንጉሣዊ የጋብቻ ልብሶቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ምልክቶች ናቸው።

ተመራማሪዎች አንደሚሉት አክሊሉ በ1740ዎቹ በእቴጌ ምንተዋብ እና ልጃቸው ንጉሥ እያሱ ወጪ የተሠራ እና ጐንደር ውስጥ ለሚገኝ ቤተክርስቲያን በስጦታ መልክ ከወርቅ ጽዋ ጋር እንደተሰጠ ያምናሉ።

እነዚህ ቅርሶች ለ146 ዓመታት በቪ ኤንድ ኤ ውስጥ ለዕይታ በቅተዋል። በ1868 እንግሊዞች ባደረጉት ውጊያ ወቅት የተወሰዱ ሲሆን ውስብስብ ታሪክም አላቸው።

የፎቶው ባለመብት, DANIEL LEAL-OLIVAS/AFP/Getty Images

በኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ 2ኛ እስር ቤት የታሰሩትን የእንግሊዝን ወታደሮች ለማስፈታት በሌተናንት ጄኔራል ሰር ሮበርት ናፒየር የሚመራ ከፍተኛ መጠን ያለው ጦር ተሰማርቶ ነበር።

የታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚሉት ከመቅደላ ቅርሶቹን ለመውሰድ በጠቅላላው 15 ዝሆኖች እና 200 ፈረሶች አስፈልገው ነበር። ከመቅደላ ተወሰዱ ተለያዩ ቅርሶች በአሁኑ ጊዜ ለበርካታ የእንግሊዝ ሙዚየሞች ተከፋፍለዋል።

ኢትዮጵያ በ2007 ብዙዎቹ ቅርሶች ሊሰጧት እንደሚገቡ ጥያቄ አቅርባለች። በሚያዝያ ወርም ቪ ኤንድ ኤ ከ150 ዓመት በፊት በእንግሊዝ ወታደሮች የተወሰዱ ቅርሶችን በውሰት ለኢትዮጰያ ለመስጠት ተስማምቷል።

ከእነዚህ ውስጥም አክሊል፣ የንጉሣዊያን የሠርግ ልብሶችና የወርቅ ጽዋ ይገኙበታል።

የቤኒን ነሐሶች

የፎቶው ባለመብት, British Museum

የቤኒን ነሐሶች የተለያዩ ቅርጻ ቅርጾች ስብስብ ሲሆን መገኛውም በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው ቤኒን የሚገኘውን የኦባ (ንጉሥ) ኦቮንራምዌንን ቤተ መንግሥትን ያስዋቡ ነበሩ።

ቅርጻ ቅርጾቹ ከዝሆን ጥርስ፣ ከነሐስ፣ ሴራሚክ እና እንጨት የተሠራ ነው። ከ15ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ኦባውን ያገለግሉ በነበሩ ባለሙያዎች የተሠሩ ናቸው።

ብዙዎቹም ለቀደምት ኦባዎች እና ንግሥት እናቶች የተሠሩ ናቸው።

ከ15ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ቤኒን በምዕራብ አፍሪካ ከሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሃገራት መካከል አንዷ ነበረች። በአውሮፓዊያኑ 1897 ቤኒን በእንግሊዝ ዲፕሎማቶችን ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ በብሪታንያ ጥቃት ደርሶባታል። በዚህም ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ ተቃጥላለች።

የንጉሣዊያን ቤተ መንግሥቱ ካለመትረፉም በተጨማሪ ህይወታቸው በአውሮፓዊያኑ 1917 እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ኦባ ኦቮንራምዌን ወደ ካላባር ሸሽተው ይኖሩ ነበር። ይህ ደግሞ የነጻይቱ የቤኒን መንግሥት መጨረሻ ምልክት ነበር።

ከዚህ ተልዕኮ መጠናቀቅ በኋላ ከነሐስ ቅርጻ ቅርጾች በተጨማሪ ሌሎችም የንጉሳዊ ቤተሰቡ ቅርሶች ተዘርፈዋል።

አንዳንዶቹ የተዘረፉት ቅርሶች በወታደሮች እጅ ሲገቡ ሌሎቹ ደግሞ ተሽጠው ወታደራዊው ተልዕኮን ለማስፈፀም የወጣውን ወጪ እንዲሸፍን ተደርጓል። የነሐስ ቅርሶቹ በመላው ዓለም ተበትነው ይገኛሉ።

የብሪቲሽ ሙዚየም በተለያዩ ሙዚየሞች በተለይም በጀርመን ሙዚየም የሚገኙ እና ከቤኒን የተዘረፉ ቅርሶችን እንዲገዙ ወኪል በመሆን መሥራቱን አስታውቋል።

በብሪቲሽ ሙዚየም የሚገኙ አብዛኛዎቹ ከቤኒን የመጡ ቅርሶች ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና ከሎርድስ ኮሚሽነርስ በአውሮፓዊያኑ 1898 የተሰጡት እንደሆነ ሙዚየሙ አስታውቋል።

ናይጄሪያ በአውሮፓዊያኑ 2021 አዲስ ሙዚየም ለመክፈት መዘጋጀቷን ተከትሎ ጥቅምት ወር ላይ የአውሮፓ ታላላቅ ሙዚየሞች ዋና ዋና ቅርሶችን በውሰት ወደ ናይጄሪያ ለመላክ ተስማምተዋል።

የናይጄሪያው ሙዚየም ነሐሶቹን ጨምሮ ሌሎች ቅርሶችን ለማሳየት ተዘጋጅቷል። ከጀርመን፣ ኔዘርላንድ፣ ስዊድን እና እንግሊዝ ተወጣጡ የሙዚየም አስተዳዳሪዎች ቅርሶቹን በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለማሳየት ተስማምተዋል።

ቮ ሰው በሊታዎ

የፎቶው ባለመብት, Field Museum of Natural History

እነዚህ በኬንያው ፃቮ አካባቢ የሚገኙ ታዋቂ ሁለት አንበሶች ናቸው። አንበሶቹ በብሪትሽ ኬንያ-ዩጋንዳ የባቡር መስመር ዝርጋታ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞችን በልተዋል።

አንበሶቹ በሞምባሳ እና ቪክቶሪያ ሃይቅ መካከል ሚገነባውን የባቡር መስመር የሚሰሩ ህንዳዊያን ላይ ለዘጠኝ ወራት ስጋት ከመፍጠር ባለፈ ግንባታው እንዲቋረጥም አስገድደው ነበር።

የፃቮ አንበሶች ከሌሎች የፃቫና አካባቢ አንበሶች ይለያሉ። ምክንያቱም ከተለመዱት አንበሶች በላይ ትልቅ ከመሆናቸውም በላይ ወንዶቹ ጎፈር አልነበራቸውም።

ባህሪያቸውም ቢሆን ለየት ያለ ነው። በአካባቢው ሚሰራውን የባቡር መስመር ተከትሎ ሠራተኞች ሲሞቱ በየቦታው ይጣሉ ስለነበር ሰዎችን በቀላሉ ለአደናቸው ይመርጧቸው ጀመር።

ሁለቱ አንበሶች በባቡር ፕሮጀክቱ በኃላፊነት ይሠራ የነበረውን የአዳኝ እና የሲቪል መሐንዲስ በነበረው እንግሊዛዊው ሌፍተናንት ኮሎኔል ጆን ፓተርሰን ተገድለዋል።

ሁለተኛው አንበሳ የሞተው በፒተርሰን 10 ጥይቶች ከተመታ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ነው። በኋላም ግለሰቡ የአደን ቦታ የጥበቃ ሠራተኛ በመሆን ማገልገል ችሏል።

አንበሶቹ ታክሲደርሚ በሚባለው ዘዴ ህይወት ያላቸው መስለው እንዲቀመጡ ቢደረግም ፓተርሰን በመጽሀፉ ከገለጸው በመጠን አነስ ብለው ነው ያሉት።

'ዘ ጎስት ኤንድ ዘ ዳርክነስ' የተባለው እና ስሙን ከሁለቱ አንበሶች ያገኘው ፊልም በአውሮፓዊያኑ 1996 ተሠርቷል።

ፓተርሰን አንበሶቹን እንደሽልማት በመውሰድ በቤቱ ለ25 ዓመታት አኑሯል። አንበሶቹ ለሌሎች ሁለት ሆሊውድ ፊልሞች፣ የምርምር እና የጋዜጣ ጽሑፎች መነሻም ሆነዋል።

ቺካጎ ኢሊዮንስ ውስጥ የሚገኘው ፊልድ ሙዚየም ኦፍ ናቹራል ሂስትሪ አንበሶቹን ከፓተርሰን በአውሮፓዊያኑ 1925 በመግዛት ከሙዚየሙ ቋሚ ስብስቦች መካከል አደረጋቸው።

ፓተርሰን አንበሶቹ የ135 የባቡር ፕሮጀክቱን ሠራተኞች እና አካበቢውን ነዋሪዎች እንደበሉ ገልጾ ነበር። ሆኖም ሙዚየሙ በኋላ ላይ በሳይንቲስቶች አደረኩት ባለው ጥናት ቁጥሩን ወደ 35 ዝቅ አድርጎታል።

ኬንያ ብሔራዊ ሙዚየም አንበሶቹ እንዲመለሱ ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የሮዜታ ድንጋይ

የፎቶው ባለመብት, AFP

በእንግሊዝ ሙዚየም የሚገኘው ሮዜታ ድንጋይ መነሻው ግብጽ ሲሆን ለየት ካለ የድንጋይ ዓይነት የተሠራ እና 1.06 ሜትር ቁመት ያለው ነው።

ድንጋዩ ከትልቅ አለት ላይ የተከፈለ ሲሆን ላዩ ላይ የተጻፈው ነገር ተመራማሪዎች የግብጻዊያንን ሄሮግላፊስ እንዲያነቡ ያስተማረ ነው።

የእንግሊዝ ሙዚም እንደሚለው ናፖሊዮን ቦናፓርት ግብጽ ውስጥ ከአውሮፓዊያኑ 1798 እስከ 1801 ድረስ ተሰማርቶ ነበር። ምሥራቃዊ ሜድትራኒያን ከመቆጣጠር ባለፈ በህንድ ላይ የበላይ በነበረችው እንግሊዝ ላይ ይዝት ነበር።

በአውሮፓዊያኑ 1799 ድንጋዩ እንዴት እንደተገኘ ባይታወቅም በናፖሊዮን ወታደሮች እንደተገኘ ግን ከፍተኛ እምነት አለ። በናይል ዴልታ በምትገኘው ራሺድ (ሮዜታ) አካባቢ ምሽግ ለመሥራት ሲቆፍሩ ነው ድንጋዩን ያገኙት።

የወታደሮቹ ኃላፊ የነበረው ፒየር-ፍራንኮስ ቡቻርድ ነው ድንጋዩ ትልቅ ቁም ነገር ያለው መሆኑን ያወቀው።

ናፖሊዮን ሲሸነፍ በአሌክሳንደሪያ ስምምነት መሠረት ድንጋዩን ጨምሮ ሌሎች በፈረንሳይ ሥር የነበሩ ቅርሶች በእንግሊዝ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

ድንጋዩ ወደ እንግሊዝ በማጓጓዝ በአውሮፓዊያኑ 1802 ፖርትስማውዝ ደረሰ። በዚያው ዓመት በጆርጅ ሦስተኛ ለእንግሊዝ ሙዚየም ተሰጠ።

ሙዚየሙ የሮዝታ ድንጋይን ለማስቀመጥ የሚሆን ጥንካሬ ስለሌለው ለዚህ የሚሆን ጊዜያዊ ቦታ ተዘጋጀ። ሌሎቹንም ቅርሶች እንዲይዝ ሌላ ማሳያ ተዘጋጀ።

ድንጋዩ በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ ሙዚየም ይገኛል።

የባንግዋ ንግ

የፎቶው ባለመብት, Dapper Foundation - Hughes Dubois

የባንግዋ ንግሥት 0.82 የምትረዝም ከእንጨት የተሰራች የካሜሮን ቅርስ ናት። ንግሥቷ የባንግዋን ህዝብ ስልጣንና ጤንነትን የሚገልጽ አቋም አላት።

ንግሥቷን ቅርስ በመላው ዓለም ከሚደነቁ የአፍሪካ ቅርሶች አንዷ ስትሆን ለካሜሮን ህዝቦች ደግሞ የጽድቅ ተመሳሌት ናት።

በቀድሞዋ ባንግዋ በአሁኗ ሌቢያልም ዲቪዥን ተምሳሌታዊ የሆኑ ምስሎች ተሠርተው ባንግዋ ንግሥት የሚል ስም ይሰጣቸዋል።

በንጉሳዊው ዘውድ ውስጥ ያላቸው ስልጣን በአንገት ጌጣቸው ላይ የሚመሠረት ነው።

የባንግዋ ንግሥት ያላት ዋጋ በሚሊዮን ዶላሮች ይገመታል። በኒውዮርክ በሚገኘው የሜትሮፖሊታን ሙዚም ካለው የባንግዋ ንጉሥ ጋር ከአፍሪካ ከተገኙ ምርጥ ቅርሶች መካከል ይጠቀሳል።

የባንግዋ ንግሥት እንዴት እንደተሰረቀች አሁንም ድረስ አይታወቅም።

የእንጨት ቅርሱ በጀርመን የቅኝ ግዛት መልዕክተኛ ጉስታቭ ኮንራው ተሰርቋል ወይም በስጦታ መልክ አግኝቶታል ተብሎ ይገመታል።

ይህ የሆነው በአሁኗ ካሜሮን ውስጥ የምትገኘውን የቀድሞዋን ባንግዋን ጀርመኖች ቅኝ ከመግዛታቸው በፊት ነው።

ቅርሱ በበርሊን ለሚገኘው ፈር ቮልከኩንድ ሙዚም ተሰጠ። በኋላ ላይ ለጨረታ ቀርቦ አሜሪካዊው የቅርስ ሰብሳቢ በአውሮፓዊያኑ 1966 ገዛው። ልጁ ደግሞ በ1990 ለዳፐር ፋውንዴሽን በጨረታ አሳልፋ ሰጠችው።

የባንግዋ ንግሥት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከካሜሮን ከወጣች በኋላ በታዋቂ የቅርስ ሰብሳቢዎች እጅ እንደገባች ታሪክ ይገልጻል።

እንደ ካሜሮናዊያኑ የባንግዋ ህዝቦች ጠበቃ ከሆነ በሃገሪቱ መንግሥትና በዳፐር ፋውንዴሽን መካከል የነበረው ድርድር ተቋርጧል። ጠበቃው እንደሚሉት የባንግዋ ህዝቦች ዋነኛ ስጋት ፋውንዴሽኑ ቅርሱን በጨረታ ለግለሰብ በማስተላለፍ እንዳይታወቅ ሊያደርግ ይችላል።

ሆኖም የአካባቢው ሰዎች ጥያቄ ከተቀረው ዓለም ትኩረት አልተሰጠውም። ዳፐር ፋውንዴሽን እንደሚለው ከሆነ ንግሥት ባንግዋ በ1990ዎቹ በጨረታ ያገኛት ንብረቱ ናት።

ከዚህ ቀደም በሄሌና ሩቢንስቴይንና ሃሪ ፍራንክሊን እጅ ነበረች።

የዚምባብዌ ወፍ

የፎቶው ባለመብት, WikiCommons

የዚምባብዌ ወፍ የተቀረጸ ወፍ ሲሆን ከታላቋ ዚምባብዌ ፍርስራሽ ቦታዎች ተገኘ ነው። ምስሉ በሃገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ገንዘቦች እና ሳንቲሞች ላይ የሚታይ አርማ ነው።

ተወዳጅ የሆኑት የወፍ ምስሎች በ12ኛውና በ15 ኛው ክፍለ ዘመን የተገነቡ ሲሆን በጥንታዊቷ ከተማ በቀደምት ሾናዎች የተሠሩ ናቸው።

ዘመናዊ ዚምባብዌ 1,800 ሄክታር ከሚሸፍነው ፍርስራሽ ነው ስያሜዋን የያገኘችው። ፍርስራሹም ከሰሃራ በስተደቡብ ከሚገኙት ትላልቅ የድንጋይ ሕንፃዎች አንዱ እንደሆነ ይገለጻል።

ቅርሱ ከጀርመን ሙዝየም በ2003 ከተላለፈ በኋላ አሁን በዚምባብዌ እጅ ይገኛል።

ሴሲል ሮሄድስ የሚባሉት የዚምባብዌ ቅኝ ገዢ እንግሊዛዊያን በ1906 የተወሰኑ ወፎች ከታላቋ ዚምባብዌ ወደ ደቡብ አፍሪካ ወስደዋል።

ደቡብ አፍሪካ በ1961 ዞምባብዌ ነጻነቷን ካወጀች በኋላ አራት ቅርሶችን መልሳለች። ይሁን እንጂ በአንድ ጀርመናዊ ሚስዮናዊ ተይዞ የነበረ አንድ ቅርስ በ1907 በበርሊን ለሚገኝ ሙዚየም ሸጦታል።

ከዚያም የሩሲያ ወታደሮች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ ጀርመንን ሲይዙ ወፉ ከበርሊን ወደ ሌኒንግራድ ተወስዶ ከቆ በኋላ የቀዝቃዛው ጦርነት ሲያበቃድረስ ወደ ጀርመን ተመለሰ።

ተወሰኑት ደግሞ በኬፕታውን በሚገኘው የሲሲል ሮዴስ መኖሪያ ቤት ይገኛሉ።