ስደተኞችን የጠለፈችው ሀንጋሪያዊቷ የካሜራ ባለሙያ ፔትራ ላስዝሎ ነፃ ወጣች

ስደተኞችን የጠለፈችው ሀንጋሪያዊቷ የካሜራ ባለሙያ ፔትራ ላስዝሎ Image copyright Reuters

በአውሮፓውያኑ 2015 የካሜራ ባለሙያ የሆነችው ፔትራ ላስዝሎ ስደተኞችን በመጥለፍና በመርገጥ ተከሳ የነበረ ቢሆንም የሀንጋሪው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነፃ አውጥቷታል።

ፔትራ ላሳዝሎ ለፈፀመችው ድርጊት ለሶስት ዓመት ያህል እግድ በመጣል የታችኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

ነገር ግን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ በወንጀል ልትጠየቅ እንደማይገባትና ከተጠየቀችም በጥቃቅን ነገር ልትጠየቅ እንደሚገባ በማሰብ በነፃ አሰናብቷታል።

ፍርድ ቤቱ ጨምሮም የፈፀመችው ድርጊት ከፍተኛ ባለመሆኑ እንደ ወንጀል ሊቆጠር አይገባም ብሏል።

አዲሷ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማን ናቸው?

"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

የቱኒዝያ አጥፍቶ ጠፊ ስራ የሌላት ምሩቅ እንደሆነች ተገለፀ

በሀንጋሪና በሰርቢያ ድንበር አካባቢ ስደተኞች ፖሊስን አምልጠው ሲሮጡ፤ ፔትራ ላሳዝሎ ህፃን ሴት ልጅን በእርግጫ ከመምታት በተጨማሪ ህፃን ልጅ ይዞ ይሮጥ የነበረ አባትን ጠልፋ ጥላለች።

በወቅቱም በመካከለኛው ምስራቅ እየተከሰተ ያለውን ግጭት ፈርተው ብዙዎች ወደ አውሮፓ የመጡ ሲሆን ከነዚህኛውም አንደኛዋ መድረሻቸው ሀንጋሪ ነበረች።

የካሜራ ባለሙያዋ የቀኝ ክንፍ ደጋፊ ለሆነው የቴሌቪዥን ጣቢያ ኤን1ቲቪ ትሰራ የነበረ ሲሆን፤ ቪዲዮውም ብዙ ተመልካች በማግኘቱ ከስራ የተባረረችው ወዲያው ነው።

ጠልፋ የጣለቻቸው አባትና ልጅ በስፔን ውስጥ ጥገኝነት ያገኙ ሲሆን ፤አባትየውም የእግር ኳስ አሰልጣኝነት ስራ ተሰጥቶታል።