“አሰልጣኝ መሆን ማለት መቃጠል ማለት ነው” - ሰውነት ቢሻው

“አሰልጣኝ መሆን ማለት መቃጠል ማለት ነው” - ሰውነት ቢሻው

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ለአፍሪካ ዋንጫ ለማብቃት ችለዋል። ለ31 ዓመታት በአሰልጣኝነት ሲያገለግሉ ለሁለት ወራት ብቻ አለመሥራታቸውን ይናገራሉ። አሁን ግን ማሰልጠን በቃኝ ብለው ትኩረታቸውን ታዳጊዎች ላይ አድርገዋል።