የጋናው የእግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት የሕይወት ዘመን እግድ ተጣለባቸው የሚሉና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

የጋናው የእግር ኳስ ፕሬዚደንት ጉቦ ሲቀበሉ

ኢትዮጵያ

ላለፉት ሶስት ቀናት ከትግራይ ወደ አማራ ክልል የሚወስደው መንገድ ቆቦ ከተማ ላይ እንደተዘጋ ነው።

የሰሜን ወሎ ዞን ፖሊስ ኦፊሰር ኮማንደር ሃብታሙ ሲሳይ እንደገለፁት መንገዱን ለመክፈት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም የአካባቢው ወጣቶች ላነሳናቸው ጥያቄዎች መልስ እንፈልጋለን በማለት እንደዘጉት ተናግረዋል።

በሰዎችም ሆነ በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ያሉት ኮማንደሩ ተሳፋሪዎች ሌላ የትራንስፖርት አገልግሎት ተመቻችቶላቸው እየተጓጓዙ ነው ብለዋል።

ደቡብ ሱዳን

በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን በጁባ የሰላም አደባባይ በመገኘት የሰላም ቀንን አከበሩ።

የአማፅያኑ መሪ ሪክ ማቻር ከሁለት ዓመት ስደት በኋላ የጁባን ምድር በዛሬዋ ዕለት ረግጠዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የተለያዩ የቀጠናው አገራት መሪዎች የተገኙ ሲሆን ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴም ንግግር አድርገዋል።

ናይጀሪያ

የናይጀሪያ ፖሊስ 400 የሚጠጉ የሺያ ሙስሊሞችን አሰረ።

ይህ የሆነው ጥቃት አድርሷል በሚል ክስ ከሶስት ዓመታት በፊት የታሰረውን መሪያቸውን እንዲለቀቅ ለመጠየቅ ያካሄዱትን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ነው።

ዛምቢያ

ዛምቢያ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ፈቃድ አግኝተው የሚሰሩ እውቅ ሴት የእግር ኳስ ዳኛን በሞት አጣች።

ሊህ ናሙኮንዳ ህይወታቸው ያለፈው በድንገተኛ የመኪና አደጋ እንደሆነ የዛምቢያ እግር ኳስ ማህበር ምክትል ፕሬዚደንት አስታውቀዋል።

ጋና

ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን በጋናው የእግር ኳስ ማህበር ፕሬዚደንት ላይ የህይወት ዘመን እግድ ወሰነ።

ይህ የሆነው 65,000 ዶላር ጉቦ ሲቀበሉ የሚያሳየው ፊልም በሚስጥራዊው ጋዜጠኛ ከተጋለጠና ላልተወሰነ ጊዜ ታግደው ከቆዩ በኋላ ነው።

አሜሪካ

አሜሪካ በየመን የሚደረገው የእርስ በርስ ጦርነት እንዲቆምና አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ።

የመከላከያ ሚኒስትሩ ጀምስ ማቲስና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙ ወገኖች በ30 ቀናት ውስጥ የተኩስ አቁም ደርሰው ችግሮቻቸውን በውይይት እንዲፈቱ አሳስበዋል።

***

በ11 ግድያዎች እንዲሁም በሌሎች በርካታ ከባድ ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆኖ የዕድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶበት በፍሎሪዳ ማረሚያ ቤት ይገኝ የነበረ አሜሪካዊው ጋንግስተር ተገደለ።

ግለሰቡ ምዕራብ ቨርጂኒያ እሥር ቤት በሌላ ታራሚ ተገድሎ መገኘቱ ታውቋል።"በፍትህ ተቋማት ላይ የለውጥ እርምጃ ይፋ ይሆናል" ጠ/ሚ ዐብይ

ህንድ

ህንድ 182 ሜትር ቁመት ያለው ለነፃነት ታጋዩ ሳርዳር የዓለማችንን ረጂሙን ሐውልት ገነባች።

ሐውልቱን ለመገንባት 430 ሚሊየን ዶላር የፈጀ ሲሆን የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር 'የአንድነት ሐውልት' ሲሉ ገልፀውታል።

የበርካታ ጎብኝዎች መዳረሻም ይሆናል ብለዋል።

ሃንጋሪ

በአውሮፓውያኑ 2015 የካሜራ ባለሙያ የሆነችው የሀንጋሪው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ስደተኞችን በመጥለፍና በመርገጥ ተከሳ የነበረችውን ፔትራ ላስዝሎቢሆንም ነፃ አውጥቷታል።

ፔትራ ላሳዝሎ ለፈፀመችው ድርጊት ለሶስት ዓመታት ያህል እግድ በመጣል የታችኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፎ ነበር።

ፓኪስታን

በእስልምና ሃይማኖት ላይ ስድብ ሰንዝረሻል ተብላ ሞት ተፈርዶባት የነበረችው የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ በፓኪስታን የሚገኝ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣቱ እንዲነሳላት ወሰነ።

አሲያ ቢቢ የተባለችው ሴት በአውሮፓውያኑ 2010 ነበር ከጎረቤቶቿ ጋር ስትጣል ነብዩ ሞሃመድን ተሳድበሻል ተብላ ክስ የተመሰረተባት።