በሴቶች ጾታዊ ትንኮሳ የተበሳጩ የጉግል ሠራተኞች ቢሮ ለቀው ወጡ

Google staff walk out

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የጉግል ሴት ራተኞች የሚያዙበት ሁኔታ ያበሳጫቸው በመላው ዓለም የሚገኙ የጉግል ራተኞች መሪያ ቤታቸውን ጥለው በመውጣት ያልታሰበ የተቃውሞ ድምጽ አሰሙ።

የጉግል ሠራተኞች ከጾታዊ ትንኮሳዎች ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ክሶች ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የጾታ ትንኮሳ ክሶችን በሽምግልና ለመፍታት የሚደረገው ጥረት እንዲቆም የጠየቁ ሲሆን፤ ይህም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት እንዲያመራ ያስችላል ተብሏል።

የጉግል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰንደር ፒቻይ ሠራተኞች መብታችሁን በመጠቀም እርምጃውን መውሰድ ትችላላችሁ በማለት ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ''የሁላችሁም ቁጭት እና ቅሬታ ይገባኛል'' ብለዋል። ለሁሉም ሠራተኞች በላኩት የኤሌክትሮኒክ መልዕክት፤ ''እኔም ስሜታችሁን እጋራዋለሁ። በማኅበረሰባችን እና በኩባንያችን ለረዥም ጊዜ በቆየው ጉዳይ ላይ ለውጦችን ለማስመዝገብ እጥራለሁ'' በማለትም አክለዋል።

የተቀውሞ ድምጻቸውን ካሰሙ የጉግል መሥሪያ ቤቶች መካከል የዙሪክ፣ የሎንዶን፣ የቶኪዮ፣ የሲንጋፖር እና የበርሊን ቅርንጫፎች ይገኙበታል።

የፎቶው ባለመብት, PA

የምስሉ መግለጫ,

ደብሊን-የአየርላንድ መዲና

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ,

ሎንዶን

የፎቶው ባለመብት, Twitter @TedonPrivacy/@googlewalkout via Reuters

የምስሉ መግለጫ,

ዙሪክ

የፎቶው ባለመብት, Walkout organisers

የምስሉ መግለጫ,

የመጀመሪያው የተቃውሞ ድምጽ የተሰማው በሲንጋፖር የጉግል መስሪያ ቤት ነበር።

የተቀውሞ ጅማሬ ምንድነው?

ባሳለፍነው ሳምንት ኒው ዮርክ ታይምስ ከጉግል ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች መካከል አንዱ፤ ጉግል የጾታ ትንኮሳ መፈጸሙን የሚያትት 'ተዓማኒነት' ያለው ክስ እንደቀረበበት እያወቀ፤ ኩባንያውን ሲሰናበት 90 ሚሊዮን ዶላር ይዞ እንዲወጣ ተፈቀደለት የሚል ዘገባ ይዞ ከወጣ በኋላ ነበር።

ክሱ የቀረበበት የአንድሮይድ 'ፈጣሪ' ነው የሚባለው አንዲ ሩቢን ይህን ክስ አይቀበልም።

ከቀናት በፊት የቀድሞ የጉግል ምርምር ጣቢያ ውስጥ የሚሰራ ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ በፍቃዳቸው ሥራ ለቀዋል። ሪቻርድ ዲቮለ የተባሉት እኚህ ሥራ አስፈጻሚ፤ በሥራ ቅጥር ቃለ መጠይቅ ወቅት በአንድ ሴት እጩ ላይ አግባብ ያልሆነ ቀረቤታ አድርገዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

ሪቻርድ ዲቮለ የሥራ መልቀቂያቸውን ካስገቡ በኋላ ምንም አይነት ምላሽ ባይሰጡም፤ ቀደም ብለው ''በተሳሳተ መንገድ ተረድተውኝ ነው'' የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ከመሥሪያ ቤታቸው የወጡት ሠራተኞች የሥራ ጠረቤዛቸው ላይ ''የሥራ ቦታዬ ላይ ያልተገኘሁት ከሌሎች የጉግል ሥራተኞች ጋር ጾታዊ ትንኮሳን፣ ያልተገቡ ባህሪዎችን፣ ግልጽነት አለመኖሩን እና ለሁሉም ያልተመቸውን መልካም ያልሆነን የሥራ አካባቢን ለመቃወም በመሄዴ ነው'' የሚል ማስታወሻ በመተው ነበር።