እንግሊዝ ውስጥ ብልትንማወፈር 100 ሺህ ብር ያህል ያስወጣል

100 ሺህ ብር፤ ብልትን ለማወፈር

የ27 ዓመቱ አብዱል ሃሳን የብልት ማስረዘሚያ መድሃኒቶች ደንበኛ ነው።

በዚህኛው ዙር ብልቱን ማስረዘም ያስፈለገው ለስምንት ዓመት አብራው የቆየችውን የፍቅር ጓደኛውን በምስራች መልክ ለማስደሰት ነው።

ባለፈው ጊዜ ብልቱን የሚያስረዝም ፈሳሽ ተወግቶ ቤታቸውን 'በፍስሃ እንደሞላው' ይናገራል።

«አንድ ጊዜ ደግሞ ባስረዝም አይጎዳኝ፤ እኔ እንጃ ብቻ ደስታ ይሰጠኛል።»

ብልት ማወፈሪያ ፈሳሽ ሲሆን በሲሪንጅ ተደርጎ ስስ በሆነው የወንድ ልጅ መራቢያ አካል በኩል ይሰጣል፤ ኦፕራሲዮን የለ፤ ምን የለ፤ በሰዓታት ውስጥ በአነስተኛ ክሊኒክ ውስጥ ሊከናወን የሚችል ነው።

ቢሆንም. . . ይላሉ ባለሙያዎች፤ ቢሆንም መሰጠት ያለበት በሙያ ጥርሳቸውን በነቀሉ ስፔሻሊስቶች እንጂ እንዲሁ አይደለም።

ይህንን ፈሳሽ አንድ ጊዜ ወደ ሰውነት ውስጥ ለማስገባት እንግሊዝ ውስጥ ያሉ ክሊኒኮች 3ሺህ ፓውንድ ይጠይቃሉ፤ ከ100 ሺህ ብር በላይ ማለት ነው።

ፈሳሹ የወንድ ልጅ ብልትን በአንድ ወይም ሁለት ሴንቲሜትር ለማወፈር የሚያስችል ንጥረ ነገር አዝሏል፤ እንደሚሰደው መጠን ደግሞ እስከ 18 ወራት ድረስ ሊቆይ ይችላል።

ችግሩ ወዲህ ነው። እኒህ ፈሳሽ ብልት ማስረዘሚያዎች ብዙ ቁጥጥር አይደረግባቸውም። ይህ ደግሞ መድሃኒቱ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንዲያይል ያደርገዋል ይላሉ ባለሙያዎች።

የእንግሊዝ የመራቢያ አካላት ስፔሻሊስት ማሕበር አባል የሆኑት አሲፍ ሙኒር «ሰዎች ይህን መድሃኒት ከመጠቀም ቢቆጠቡ ይሻላል» ይላሉ።

«መድሃኒቱ ብልትን ከማርዘም ይልቅ ኋላ ላይ የሚያመጣው መዘዝ የከፋ ነው» ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

ምንም የሚደበቅ ነገር የለም. . .

አብዱል በራስ መተማመኑ ዝቅ ማለቱ መድሃኒቱን እንዲጠቀም እንዳስገደደው ይናገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ መድሃኒቱ ወደሰውነቱ ሲገባ የራስ መተማመንን ይዞ እንደገባ ይናገራል፤ ኋላ ላይ መዘዝ እንዳይመጣበት ፍራቻ ቢጤ ወረር እንዳደረገው ባይክድም።

«ልክ መድሃኒቱን ስወስድ በራስ መተማመን በውስጤ ሲሰራጭ ይሰማኛል፤ ምንም የሚደበቅ ነገር የለም።»

እንግሊዝ የመድሃኒቱ ፈላጊ ዜጎቿ ቁጥር ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ከሰባሰበችው ጥናት ማወቅ ችላለች።

ከሦስት ዓመታት በፊት በወር ቢበዛ 10 ሰዎች ብቻ ናቸው የሚጠቀሙት፤ አሁን ግን ቁጥር ወደ 700 ገደማ ደርሷል።

ባለሙያዎች እጅግ ያስጨነቀው ጉዳይ ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው መውጋት መጀመራቸው ነው።

ሙኒር እንደሚሉት ሰዎች ቫዝሊንና ሌሎች መሰል ቅባቶችን በመጠቀም ራሳቸውን ይወጋሉ፤ ይህ ደግሞ መዘዙ የከፋ ነው።

«እንዲህ ያደረጉ ተጠቃሚዎች ቁስለት ስለሚያጋጥማቸው ከቀናት በኋላ ወደ ህክምና ጣቢያዎች መምጣታቸው አይቀርም» ይላሉ ባለሙያው።

«እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያጋጥመን ብዙ ጊዜ የምናደርገው የብልትን ሽፋሽፍት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ ከሌላ የሰውነት ክፍል በሚገኝ ቆዳ መተካት ነው።»

ስቱዋርት ፕራይስ ይህን ህክምና ወደሚሰጡ ክሊኒኮች ሲያመራ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፤ የ36 ዓመቱ ጎልማሳ ወንዶች ሁሉ እኮ ተለቅ ያለ ብልት ቢኖራቸው ይመርጣሉ ይላል።

«እኔ መድሃኒቱን ባልጠቀመውም ግድ የለኝም፤ ነገር ግን የልብ ልብ እንዲሰጠኝ ነው ልሞክረው የወሰንከት። ትንሽ ተለቅ ቢልልኝ አልጠላም» ይላል።

ስቱዋርት በይነ-መረብ ላይ ተተክሎ ፀጉር አሳዳጊ ምርቶችን በመቃኘት ላይ ሳለ ነበር ቀዶ ጥገና የማይጠይቀውን የመድሃኒቱን ጉድ ያነበበው።

2015 ላይ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው የወንድ ልጅ ብልት ለወሲብ ሲነሳሳ መካከለኛ ርዝመት 13 ሴንቲሜትር (5.1 ኢንች) ነው።

ጥናቱ በዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 15 ሺህ ወንዶችን አካቶ የተሠራ ነው።

የምስሉ መግለጫ,

የስቱዋርት ፍቅረኛ ካሪስ

ስቱዋርት 15 ሚሊ ሌትር ማስረዘሚያ ፈሳሽ ለመወሰድ ተዘጋጅቷል፤ ክሊኒኮችም ቢሆን ከዚህ በላይ ማስረዘሚያ እንዲወሰድ አይመክሩም።

የስቱዋርት ፍቅረኛ ካሪስ ጭንቀት ቢጤ ወሯታል፤ እንደው የጓደኛዋ ብልት መጠን ከልክ እንዳያልፍ በማለት።

ፈሳሹ ከመጠን በላይ ሆኖ ቢገኝ ወደ ክሊኒክ ተመልሶ ማስቀነስ ይቻላል፤ ያው ሌላ ወጪ ቢሆንም።

ምንም እንኳ ካሪስ በጭንቀት ብትዋጥም ሂደቱ ቀጠለ፤ ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላ ውጤት ለማየት የብልቱ ውፍረት መጠን መለካት ነበረበት።

የስቱዋርት ብልት ውፍረት መጠን ከ12.5 ወደ 15 ሴንቲሜትር ደረሰ፤ ስቱዋርትም «ትልቅ የሆንኩ ያህል ተሰማኝ፤ ደስታም ወረረኝ» ሲል ተሰማ።

ዶክተሮች የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ከተወጉ በኋላ ቢያንስ ለአራት ሳምንታት ወሲብ እንዳያደርጉ ይመክራሉ፤ ውፍረቱ ከ10 ሴንቲሜትር ወደ 11 የደረሰለት አብዱል «ዋናው መጠኑ መተለቁ ነው እንጂ. . .» ይላል።

«መቼም የጤና እውክ እንዲገጥም አትፈልግም» የሚለው አብዱል ከአፍታ ዝምታ በኋላ «በተለይ ደግሞ ከመራቢያ አካል ጋር በተያያዘ» ሲል ያክላል።