በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ውስጥ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ 10 ሰዎችን ገደለ

የወባ ትንኝ Image copyright Bob Chamberlin

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቢጫ ወባ ምክንያት አስር ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት በሽታውን ለመከላከል የሚያግዝ ክትባት እያቀረበ መሆኑን ገለፀ።

በዚህ አደገኛ በሆነውና በወባ ትንኝ አማካይነት በሚከሰተው በሽታ ሰዎቹ ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ድርጅቱም ለቢጫ ወባ የሚሆን ክትባት ለአስቸኳይ ጊዜ ካዘጋጀው ክምችቱ በማውጣት እንያቀርበ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

ጫትን መቆጣጠር ወይስ ማገድ?

ወረርሽኙ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ከሁለት ወራት በፊት በታመመ አንድ ግለሰብ ላይ የተገኘ ሲሆን፤ 35 የሚሆኑ በቢጫ ወባ ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎችም ተገኝተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት እንዳለው "ለበሽታው ባለ ከፍተኛ ተጋላጭነትና በክትባት እጦት ሳቢያ የቢጫ ወባ ወረርሽኝ መከሰቱ አሳሳቢ ሆኗል።"

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ የጡንቻ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ ትውከትና የሰውነት መዛል ምልክቶች የሚታዩባቸው ሲሆን የተወሰኑት ላይ ደግሞ ጠንከር ያሉ የህመም ምልክቶች ይታያሉ። በበሽታው ከተያዙት መካከል ግምሽ የሚሆኑት ከሰባት እስከ አስር ቀናት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይሞታሉ።

አትክልት ብቻ ስለሚመገቡ ሰዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች

Image copyright CRISTINA ALDEHUELA

በወላይታ ዞን በተከሰተው ይህ የቢጫ ወባ ወረሽኝ ሙሉ ለሙሉ የተመዘገበው ኦፋ ወረዳ ውስጥ ሲሆን ከክስተቱ በኋላ በተካሄደ የመከላከያ ክትባት ዘመቻ ተጨማሪ ሰዎች በበሽታው አለመያዛቸው ተገልጿል።

ቢሆንም ግን የዓለም የጤና ድርጅት በከፊል በአካባቢው ባለ ግጭት ምክንያትነት በሽታው ሊስፋፋ የሚችልበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል አመልክቷል። ጨምሮም 1.45 ሚሊዮን የሚደርስ ክትባት በስፋት መካሄድ ላለበት የክትባት ዘመቻ "ያለምንም ተጨማሪ መዘግየት" እንዲቀርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

ተፈጥሮን በብሩሽ የሚመዘግበው መዝገቡ

ኢትዮጵያ የቢጫ ወባ በስፋት በሚከሰትበት መልክአ ምድር የምትገኝ ስትሆን እስከ 1960ዎቹ ድረስ ተደጋጋሚ ወረርሽኝ አጋጥሟት ነበር። በፈረንጆቹ 2013 በደቡብ ክልል 143 ህሙማን እስከተመመዘገቡበት ክስተት ድረስ ችግሩ እንዳልታየ የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።

የቢጫ ወባ መከላከያ ክትባትን ከመደበኛ ክትባቶች ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመስጠት ዕቅድ አለ።