በፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር አሲረዋል የተባሉ ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን Image copyright Getty Images

የፈረንሳይ ባለስልጣናት በፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ሲያሴሩ ነበር ያሏቸውን ስድስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አስታወቁ።

ማንነታቸው ያልተገለጸው 5 ወንዶች እና አንዲት ሴት በቁጥጥር ሥር የዋሉት በሰሜን ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ መሆኑን ባለስልጣናቱ ጨምረው ገልጸዋል።

ለፍርድ ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ''ወንጀለኛ የሽብር ቡድን ማሕበር'' የሚል ምረመራ ተጀምሮባቸዋል ሲሉ ተናግረዋል።

''ትራምፕ በሶሪያ እንዲቆዩ አሳምኛቸዋለሁ'' ማክሮን

ፈረንሳይ ስደተኞችን የተመለከተ ጥብቅ ሕግ አወጣች

የተጠርጣሪዎቹ ማንነትም ሆነ ያሴሩት ሴራ ዝርዝር ለህዝብ ይፋ አልሆነም።

ተጠርጣሪዎቹ ረዘም ላለ ጊዜ በፈረንሳይ መንግሥት የቅርብ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበረ የሃገር ውስጥ ደህንነት ቢሮ አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ምስራቅ ፈረንሳይ ውስጥ የ1ኛ የዓለም ጦርነት የውጊያ ስፍራዎችን እየጎበኙ ሳለ ነው ይህ ዜና የተሰማው።

በተመሳሳይ መልኩ ከአንድ ዓመት በፊት የ23 ዓመት ወጣት ፕሬዚዳንት ማክሮንን ለመግደል አሲረሃል ተብሎ በቁጥጥር ሥር ውሎ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ