ዲዲየር ድሮግባ ከእግር ኳስ ጨዋታ እራሱን ማግለሉን የተመለከቱና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

Image copyright Julian Finney

ኢትዮጵያ

• በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሰመረ ርዕሶም የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አቀረቡ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም የሹመት ደብዳቤ ቅጂውን የተቀበሉ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ግንኙነት ዙሪያም ውይይት አድርገዋል።

• የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገቡ።

በአሜሪካ ሲኖሩ የነበሩት የህግ ባለሙያዋ ከሰባት ዓመት ቆይታ በኋላ ነው ወደ ሀገራቸው የተመለሱት።

"የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው" ጄኔራል አሳምነው

ኮትዲቯር

• እውቁ እግር ኳሰኛ ዲዲየር ድሮግባ ከእግር ኳስ ጨዋታ እራሱን አገለለ።

የ40 ዓመቱ ኮትዲቯራዊ አሜሪካ ውስጥ ፊኒክስ ራይዚንግ ለሚባል ቡድን በመጫወት ላይ ነበረ።

ዚምባብዌ

• ዚምባብዌ ውስጥ ሁለት የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎች ተጋጭተው 47 ዜጎች ህይወት አለፈ።

ከሟቾች መካከል ሁለት ህጻናት ሲገኙበት፤ ሌሎች 70 ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

"ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም" ብርቱካን ሚደቅሳ

ቦትስዋና

• ቦትስዋና ውስጥ ከ400 መቶ በላይ የሚሆኑ ጎሾች ቾቤ የተባለ ወንዝ ውስጥ ሰምጠው ሞቱ።

ጎሾቹ ከአንበሳ መንጋ ለማምለጥ ባደረጉት ሽሽት አደጋው ሳይከሰት እንዳለቀረ ተገምቷል።

አሜሪካ

• በአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት የምሽት መዝናኛ ቤት ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት አንድ ፖሊስን ጨምሮ 12 ሰዎች ተገደሉ።

የጥቃቱ ፈጻሚ ማንነት ያልተገለጸ ሲሆን፤ በቦታው እራሱን ሳያጠፋ እንዳልቀረ ፖሊስ ገልጿል።

ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት የሃገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው

ደቡብ ኮሪያ

• ግዙፉ የተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች ሳመሰንግ መተጣጠጠፍ የሚችል ስልክ አስተዋወቀ።

ተንቀሳቃሽ ስልኩ ከቀጣዩ ወር ጀምሮ መመረት እንደሚጀምር ድርጅቱ አስታውቋል።

እንግሊዝ

• እንግሊዝ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እስካሁን ድረስ ጥቁርና ነጭ ቀለም ያለው ቴሌቪዥን እንደሚጠቀሙ ተገለጸ።

ምንም እንኳን በአውሮፓውያኑ 1967 ባለ ቀለም ቴሌቪዥኖች ቢተዋወቁም እነዚህ ሰዎች ተጠቅመውት አያውቁም ተብሏል።

ሆላንድ

• ሆላንዳዊው ጡረተኛ ወጣት ሴቶችን ለማማለል እንዲመቸው እድሜውን በ20 ዓመት ዝቅ ለማድረግ ፍርድ ቤት ሄዷል።

ሰውዬው ዕድሜን መቀየር ለምን አይቻልም ያለ ሲሆን፤ ጉዳዩን የያዘው የአካባቢው ፍርድ ቤት በቀጣዮቹ አራት ሳምንታት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

የካቢኔ አባላት በፌስቡክ ማስታወቂያ ተመረጡ

ኢራቅ

• የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱል ማህዲ አምስት የካቢኔ አባላታቸውን ከ15 ሺ ሰዎች መካከል በበይነ መረብ አወዳድረው መረጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ወር ነበር ብቁ ነን ብለው የሚያስቡ ተወዳዳሪዎች ሲቪያቸውን በበይነ መረብ በኩል እንዲያስገቡ የጠየቁት።

ተያያዥ ርዕሶች