ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሞቃዲሾ በረራ መጀመሩን የተመለከቱና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

Image copyright AFP

ኢትዮጵያ

• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መኪና እያሽከረከሩ የኤርትራንና የሶማሊያ መሪዎችን ባህርዳርን አስጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ የጎንደር ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ባህር ዳር ከተማ ገብተዋል።

• በኢትዮጵያ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታ ላይ የ200 ሰዎች የጅምላ መቃብር ማግኘቱን ፖሊስ አስታወቀ።

የጅምላ መቃብሩ የተገኘው ከቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ሞሃመድ ክስ ጋር ተያያዙ መረጃዎችን በማሰባሰብ ወቅት እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ ወደ ሶማሊያ በረራ ጀመረ

• የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ41 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ዛሬ ወደ ሶማሊያዋ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በረራ ጀመረ።

የመጀመሪኣው በረራ አውሮፕላን ሞቃድሾ ሲደርስ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል አደርገዋል።

ታንዛኒያ

• ትላንትና በታንዛኒያ ቾቤ ወንዝ ውስጥ ሰጥመው የሞቱት 400 ጎሾች ስጋ በአካባቢው ነዋሪዎች መወሰዱ ተገለጸ።

የሃገሪቱ የአካባቢ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በወንዙ አቅራቢያ ያሉ ሰዎች የጎሾቹን ስጋ ለምግብነት እንዲጠቀሙት ተፈቅዶላቸዋል።

ናይጄሪያ

• ናይጄሪያ ውስጥ አንድ ከፍተኛ የመንግስት እስረኛ ወርሃዊ የምግብ ወጪው 3.5 ሚሊዮን የናይጄሪያ ናይራ እንደሆነ ተዘገበ።

መረጃውን ይዞ የወጣው የቴቪዥን ጣቢያ መረጃውን እውነት ቢሆንም ትክክለኛ ባለሆነ መነረገድ ነው ያገኘሁት በማለት ይቅርታ ጠይቋል።

በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ ድንበር ላይ የጅምላ መቃብር ተገኘ

አሜሪካ ለህገ ወጥ ስደተኞች ጥገኝነት መስጠት ልትከለክል ነው

ፈረንሳይ

• ራይንኤይር የተባለው አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ፈረንሳይ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ።

አየር መንገዱ ለፈረንሳይ መክፈል የነበረበት 600 ሺ ዶላር ካልከፈለ አውሮፕላኑ እንደማይለቀቅለት የሃገሪቱ አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቋል።

አሜሪካ

• ከዚህ በኋላ በሜክሲኮ ድንበር በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ህገወጥ ስደተኞች ጥገኝነት ማግኘት አይችሉም ሲሉ ባለስልጣናት አስታወቁ።

ማንኛውም ግለሰብ በሜክሲኮ ድንበር በሕገወጥ መልኩ የሚገባ ከሆነ ጥገኝነት ቢጠይቅም ማግኘት የማይችል ሲሆን፤ ህጉ ተግባራዊ የሚሆነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲፈርሙበት ነው።

ስዊድን

• አንድ ስዊድናዊ እንግሊዝ ውስጥ ለሚገኝ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በላከው ጥቅል መልእክት ውስጥ ቤት ሰራሽ ቦምብ በማስገባቱ የ6 ዓመት እስር ተፈረደበት።

ሰውዬው የይለፍ ቃል አንቀይርልህም በመባሉ ነው ቦምቡን በፖስታ አሽጎ የላከው።

ሲቲ ከዩናይትድ፤ ማን ያሸንፍ ይሆን?

• በዓለማችን የሚገኙ ሴቶች የሚወልዷቸው ልጆች ቁጥር እጅጉን እንደቀነሰ የዘርፉ ተመራማሪዎች ገለጹ።

ቀደም ባሉት ዓመታት እናቶች በአማካይ 4.7 ልጆች የሚወልዱ የነበረ ሲሆን፤ አሁን ግን በግማሽ ቀንሶ ቁጥሩ 2.4 ደርሷል።

ተያያዥ ርዕሶች