ህንዳዊው ያልተገባ ቀልድ በመቀለዱ ለእስር ተዳረገ

አብሂጂት ኢየር- ሚትራ Image copyright FB
አጭር የምስል መግለጫ አብሂጂት ኢየር- ሚትራ

በህንዷ ከተማ ደልሂ መሰረት ባደረገውና የመከላከያ ኃይል ባለሙያ የሆነው አብሂጂት ኢየር- ሚትራ ካሳለፍነው መስከረም ወር በምስራቃዊው ኦሪሳ ግዛት የሚገኘውን የ13ኛው ክፍለ ዘመን ኮናርክ ቤተ መቅደስ ሲጎበኝ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል "የሚያጣጥልና እርባና የሌለው" ሲል በትዊተር ገፁ ላይ ለጥፎታል።

ግለሰቡ 20 ሺህ የትዊተር ተከታዮች አሉት።

በዋትስ አፕ ሐሰተኛ ወሬ ተቃጥለው የተገደሉት

ለእስር የተዳረገው ቤተ መቅደሱ ላይ ያልተገባ አስተያየት በመፃፉ ነበር፤ ምንም እንኳን የፃፍኩት ቀልድ ነው ቢልም ጆሮ የሰጠው የለም ።

ከዚህ ባሻገርም በመንግሥትና በሌላ ቤተ መቅደሶችን በተመለከተ የፃፈው ተደጋጋሚ ቀልዶች እንዲሁ ሰዎችን ለማሳቅና ለማዝናናት ያደረገው እንደሆነ ተናግሯል።

ፖሊስ እንደገለፀው ቅሬታ ያቀረቡት ሰዎች 40 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ የሚኖርባትን ኦሪሳ ግዛት ነዋሪዎችን ስሜት የጎዳ ነው ብለዋል።

የሚያመልኩበትን ስፍራም እንደዚያ በማጣጣሉ በርካቶች እንደተቆጡ ጨምሮ ገልጿል።

ቤተ መቅደሱ የታወቀና ታሪካዊ ነው፤ በዚህ ላይ እንዴት ይዘባበትበታል ሲሉ ስሜታቸውን የገለፁም አሉ።

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ፡ ‘‘ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ’’

በተከታዮቹ ዘንድ ቁጣን በመጫሩም ግለሰቡ በትዊር ገፁ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ አስተያየት የሰጠው አልነበረም፤ አንድ ጊዜ በለጠፈው ፅሁፍ የወደዱት ሰባት ሰዎችና አስተያየትም የሰጠው አንድ ግለሰብ ብቻ ነበር።

ይሁን እንጂ በግዛቱ በሚኖሩ የተለያዩ ባህልና ሃይማኖት ያላቸው ሰዎች መካከል ቁርሾ የሚፈጥር ድርጊት በመፈፀሙ እንዲሁም በሃይማኖት ላይ በማፌዙና ለበርካታ ሰዎች ቁጣ መነሻ በመሆኑ ክስ ሊመሰረትበት ችሏል።

በህዝብ ሃሳብ መለዋወጫ በሆነው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጸያፍ ድርጊት በማስተላለፉ ጭምር ጥፋተኛ ተብሏል።

የአገሪቱ የቅርስ አጠባበቅ ህግም ቤተ መቅደሱን ላልተገባ ዓላማ በመጠቀሙ እንደሚያስቀጣው ሲያትት፤ የመረጃና ቴክኖሎጂ ህግ ደግሞ ቁጣን የሚያጭር ያልተገባ መልዕክት በማስተላለፉ እንዲቀጣ ያዛል።

የ7 ዓመቷ ህጻን ግድያ፡ ''ከልክ ያለፈ ቅጣት የልጄን ህይወት አሳጣኝ''

ኢየር ሚትራ የቤተ መቅደሱን ገፅታ በማበላሸት (ስም በማጥፋት) ወንጀል ቢያንስ 5 ዓመት እስር ሊጠብቀው እንደሚችልም ተገልጿል።

ግለሰቡ ለሰራው ጥፋት ይቅርታ እንዲደረግለት ቢለምንም ፖሊስ ክስ መስርቷል፤ ፍርድቤቱም ማስረጃ እስከሚጠናከር ድረስ በገንዘብ ዋስ መውጣት እንደማይችል ገልጿል።

ውሳኔው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን የሚፃረር ነው ሲሉ የተቃወሙትም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አልጠፉም ታዲያ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ