ህንድ ውስጥ የ12 ቀን ጨቅላ በጦጣ ተነክሶ ህይወቱ ማለፉን የተመለከቱን ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

Image copyright Getty Images

ዩጋንዳ

የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የቻይናውያን የንግድ ድርጅቶችን የሚጠብቅ ወታደራዊ ግበረ ሃይል እንዲሰማራ አዘዙ።

በቅርቡ ከ120 በላይ ቻይናውያን ባለሃብቶች ንብረታችን ተዘርፎብናል ማለታቸው ይታወሳል።

ማላዊ

በማላዊ የምትገኝ ነርስ በማዋለጃ ክፍል ውስጥ የተነሳችውን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ በመልቀቋ ከስራ ታገደች።

የሃገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሲናገሩ ምስሉ እጅግ ዘግናኝ ነበር ብለዋል።

የደህንነት ተቋሙ ምክትል የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ፍርድ ቤት ቀረቡ

በሞያሌ በተከሰተ ግጭት የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

ናይጄሪያ

የናይጄሪያ ባለስልጣናት ዝቅተኛው የሰራተኞች ደሞዝ ወደ 30 ሺ ናይራ ከፍ እንዲል የተደረሰውን ስምምነት ውድቅ አደረጉት።

የሰራተኛ ማህበራቱ ያቀረቡት ሃሳብ መንግሥትን ተጨማሪ 82 ሚሊዯን ናይራ ስለሚያስወጣን አንችልም ብለዋል።

ህንድ

ህንድ ውስጥ አንድ የ12 ቀን ጨቅላ በዝንጀሮ ተነክሶ ህይወቱ አለፈ።

እናትየው በወቅቱ ጡት እያጠባችው የነበረ ሲሆን፤ ዝንጀሮው ወደ ቤት በመግባት ነው ህጻኑን ነጥቆ የሮጠው።

ፊሊፒንስ

የፊሊፒንሱ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴሬዝ በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ከሚመክረው ስብሰባ በእንቅልፍ ምክንያት መቅረታቸው ተገለጸ።

የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት እንደገለጸው ዱቴርቴ እረፍት ለማድረግ ሲሉ አራት ውይይቶች አምልጠዋቸዋል።

ህንዳዊው ያልተገባ ቀልድ በመቀለዱ ለእስር ተዳረገ

ማላዊቷ ነርስ በማዋለጃ ክፍል 'ሰልፊ' በመነሳቷ ከስራ ታገደች

እንግሊዝ

እንግሊዝ ውስጥ ከሁለት ሳምነት በፊት 76 ሚሊዮን ፓውንድ የደረሰው የሎተሪ እድለኛ የገባበት አልታወቀም።

የሎተሪው አዘጋጆች እድለኛው እስከ ፊታችን ግንቦት የማይመጣ ከሆነ ገንዘቡን ተመላሽ እናደርጋለን ብለዋል።

ጃፓን

የጃፓኑ የበይነ መረብ ደህንነት ሚኒስትር ዮሺታካ ሳኩራዳ በህይወታቸው ኮምፒውተር ተጠቅመው እንደማያውቁ ገለጹ።

ባለፈው ወር የተሾሙት የ68 ዓመቱ ሚኒስትር ገና ካሁኑ የመምራት ብቃታቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።

አሜሪካ

ታዋቂው የተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች አፕል የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ ለሆኑ ተጎጂዎች ስራ ሊሰጥ ነው።

ሰዎቹ ማንነታቸው ለድርጅቱም ቢሆን የማይገለጽ ሲሆን ጉዳዩን የሚከታተል አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ይኖራል።

ኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተነሳ

አዲስ ፍቅረኛውን ፓሪስ ለመውሰድ ከቀድሞ ፍቅረኛው ገንዘብ የሰረቀው ግለሰብ

ሳኡዲ አረቢያ

ታዋቂው ጋዜጠኛ ጃማል ካሾግጂ የተገደለው በአንድ የደህንነት ሃላፊ ትእዛዝ እንጂ በሳኡዲው ልዑል ሞሃመድ ቢን ሰልማን እንዳልሆነ የሳኡዲ አቃቤ ህግ ገለጸ።

በተጨማሪም ሃላፊው የራሱን ቡድን በማዋቀር ወደ ቱርክ የተጓዘው ካሾግጂን ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለማምጣት ነበር ብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች