የካሊፎርኒያው ሰደድ እሳት፡ የጠፉ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ጨመረ

በሰደድ እሳቱ የወደመው ከፊል ገፅታ

በካሊፎርኒያ ሰሜናዊ አካባቢ በተነሳ ሰደድ እሳት በርካታ ሰዎች መጥፋታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ቁጥራቸውም ከ600 ሊበልጥ እንደሚችል የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

ትናንት በአደጋው 7 ተጨማሪ ሰዎች ሞተው መገኘታቸውም ታውቋል፤ ከትናንት ጀምሮ የጠፉ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩም ተገልጿል።

በካምፕ ውስጥ በተቀሰቀሰው በዚህ ሰደድ እሳት በትንሹ 63 ሰዎች ሲሞቱ ወደ 12 ሺህ የሚጠጉ ህንፃዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በደቡባዊ ግዛቷ ውልስይ ሌላ 3 ሰዎች ሕይወታቸውን አልፏል።

ካሊፎርኒያ እየተቃጠለች ነው

ከ150 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም

በግዛቷ 9 ሺ 400 የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው።

ይሁን እንጂ የአካባቢው ባለስልጣን ሸሪፍ ኮሪይ ሆኒያ በሰጡት መግለጫ የተጎጂዎች ቁጥር ሊለዋወጥ ይችላል ብለዋል።

የግዛቷ የእሳት አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ መስሪያ ቤት ኃላፊ ኬም ፒምሎት በበኩላቸው እስካሁን 40 በመቶ የሚሆነውን እሳት መቆጣጠር እንደተቻለና ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በሞያሌ በተከሰተ ግጭት የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ

58 ሺህ 679.47 ሔክታር የሚሆነውን በእሳት የተያያዘ ክፍል በአንድ ጊዜ ለመቆጣጠር አዳጋች በመሆኑ ሊፈታተናቸው እንደሚችል ኃላፊው ስጋታቸውን አስረድተዋል ።

የአገሪቱ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ አስተዳዳሪ ብሮክ ሎንግ "በሕይወቴ ያየሁት አሰቃቂ አደጋ ነው" ሲሉ የአደጋውን አስከፊነት ገልፀዋል።

ከስምንት ቀናት በፊት ካምፕ ውስጥ የተነሳው እሳት በንፋስ በመታገዝ ወደ ሰሜን አቅጣጫ በፍጥነት የተዛመተ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ስፍራውን ለቀው እንዲወጡ ፋታ አልሰጣቸውም ነበር።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን ለመጠየቅና የጉዳቱን መጠን ለመጎብኘት ነገ ወደ ስፍራው ያቀናሉ።

እስካሁን የእሳቱ መነሻ ምክንያት በውል አልታወቀም።