የነጻነት ቅርጫት: ሊፕስቲክ

Lipstick image
ተጨማሪ ከዚህ በታች ያንብቡ
ሌላ መሣሪያ ለመምረጥ ይህን ይለፉ

በቅርቡ በሃገር አሜሪካ የተካሄደ ጥናት እንደጠቆመው ወደ ስራ ቦታ ከማቅናታቸው በፊት ሊፕስቲክ የሚቀቡ ሴቶች ከማይቀቡት የተሻለ ይከፈላቸዋል።

የውበት መጠበቂያ ምርት ኢንዱስትሪ በዓመት $500 ቢሊዮን ያንቀሳቅሳል። ተቺዎች የውበት መጠበቂያ ምርት ማስታወቂያዎች ከእውነታው የራቀ ውበት እንደሚያጎናጽፉ ተደርገው ይቀርባሉ ይላሉ።

በአንዳንድ የእስያ ሃገራት ቆዳን የሚያነጡ ምርቶችም ለገበያ ይውላሉ።

ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ።

በተጨማሪም ማስታወቂያዎቹ ላይ የሚስተዋሉት የሞዴሎች መልክ በብዙ መልኩ ተቀናብሮ የሚቀርብ ሲሆን፤ ሴቶች እራሳቸውን ከሞዴሎቹ ጋር እንዲያነጻጽሩ ይደረጋሉ ይላሉ።

የመጀመሪያዎቹ የሊፕስቲክ ተጠቀሚዎች ለፖለቲካ ተሳትፎ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ አሜሪካውያኖች እንደሆኑ ይገመታል። ዛሬ ላይ ሴቶች ምንም አይነት የመዋብያ ምርት ሳይጠቀሙ እራሳቸውን ፎቶግራፍ (ሰልፊ) በማንሳት የማሕብረሰቡን አስተሳሰብ እየተጋፈጡ ይገኛሉ።