የነጻነት ቅርጫት፡ ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ

High heels image
ተጨማሪ ከዚህ በታች ያንብቡ
ሌላ መሣሪያ ለመምረጥ ይህን ይለፉ

በርካታ ጥናቶች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማዎችን መጫማት የሰውነት ጡንቻ እና አጥንት ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ይጠቁማሉ። ጫማዎቹ ምቾት ስለሚነሱ ተጨማሪ የጫማ ሶል እና ሌሎች ምርቶችን ለመግዛት ያስገድዳሉ።

ምናልባትም ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ አለመጫማት የተሻለ ይሆን?

በአሁኑ ሰዓት ሴቶች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማዎችን ለመዘነጫነት ቢጫሟቸውም በቀድሞው መጠሪያዋ ፐርሺያ በአሁኗ ኢራን ባለረዥም ታኮ ጫማ ይጫሙ የነበሩት ወንዶች እንጂ ሴቶች አልነበሩም። የኢራን ፈረሰኛ ወንድ ወታደሮች በጦርነት ወቅት የጫማቸው ታኮ ሚዛናቸውን እንዲጠብቁ ይረዳቸው ነበር።

ከእነዚህ ምርጫዎች መካከል የሚፈልጉትን ዕቃ ይምረጡና እንዴት የጭቆና መሣሪያ እንደሆነ ይመልከቱ።

2016 ላይ የአንድ ተቋም እንግዳ ተቀባይ ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ እንድትጫማ በአሰሪዎቿ ብትታዘዝም ፍቃደኛ ሳትሆን ሥራዋን በገዛ ፍቃዷ ለቃለች። ከዚያም የእንግሊዝ መንግሥት ሰራተኞች ባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ መጫማት ግዴታ እንዳይሆን ህጉ እንዲቀየር ጠይቃ ነበረ። የእንግሊዝ መንግሥት ግን ህጉን ባይቀይረውም በስራ ቦታዎች ላይ የሰራተኞችን የአለባበስ ስርዓት በተመለከተ ማስተካከያዎችን አደርጋለሁ ብሎ ነበር።