የተባበሩት መንግሥታት ስደተኞች በየዓመቱ 8 ቢሊዮን ዶላር ለቤተሰቦቻቸው ይልካሉ ይላል

አንዲት ስደተኛ ወይን ስትለቅም Image copyright PA

በእንግሊዝ በተለያዩ ስራዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ስደተኞች ካጠራቀሙት ገንዘብ በዓመት የሚልኩት እስከ 8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ድርጅት አስታወቀ።

አብዘኛው ገንዘብ ለህጻናት ትምህርት ቤት ክፍያ የሚውል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ በጣም ደሃ ወደ ሆኑ ሃገራት ነው ተብሏል።

ድርጅቱ እንዳስታወቀው እነዚህ ስደተኞች ከሚልኩት ገንዘብ ውስጥ ትንሽ የማይባል መጠን ያለው ገንዘብ ለአለማቀፍ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች ይከፈላል።

ምንም እንኳን ዓለማቀፍ ህጉ ለገንዘብ ዝውውር ከ3 በመቶ በላይ መከፈል የለበትም ቢልም፤ ስደተኞቹ እስከ 7 በመቶ ድረስ እንዲከፍሉ እንደሚደረግ የተባበሩት መንግስታት ገልጿል።

ወሎ በነዳጅ 'ልትባረክ' ይሆን?

85 ሺ የየመን ህጻናት በምግብ እጥረት ሞተዋል

በእንግሊዝ የሚገኘው የክፍያ ስርዓት ማዕከላት ሕብረት እንደሚለው የዓለምአቀፍ ማዘዋወሪያ ክፍያዎች በጣም እየናሩ የመጡት አገልግሎቱን የሚሰጡ ድርጅቶች ቁጥር ትንሽ በመሆኑ ነው ይላል።

እንግሊዝ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን በማስተናገድ ትልቅ ድርሻ ያላት ሲሆን፤ ናይጄሪያውያን፣ ህንዳውያንና ፓኪስታናውያን በቢሊዮን የሚቆጠር ፓውንድ ወደ ሃገር ቤት በመላክ ቀዳሚዎቸ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ፓውንድ ደግሞ ወደ ፖላንድ፣ ቻይና፣ ኬንያ፣ ፊሊፒንስ፣ ባንግላዲሽና ጋና ይላካል።

ከአሜሪካ የሚላክ ከፍተኛ መጠን ያለው ዶላር ደግሞ መዳረሻው የማዕካለዊ አሜሪካና ደቡባዊ አሜሪካ ሃገራት ናቸው።

ምንም እንኳን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ያደጉት ሃገራት ገንዘብ ወደ ደሃ ሃገራት ቢላክም፤ በጣም ብዙ ሊባል የሚችል ገንዘብ ደግሞ በአዘዋዋሪዎችና ባንኮች ይወሰዳል።

ስደተኞቹ ለዓለማቀፍ የገንዘብ ዝውውር የሚከፍሉት ገንዘብ እስከ 3 በመቶ ድረስ ዝቅ ቢል በየዓመቱ የሚላከው ገንዘብ ላይ ተጨማሪ 25 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት ይቻላል።

ይህ ማለት ደግሞ ተጨማሪ 1 ቢሊዮን ዶላር የህጻናት ትምህርት ላይ ይውላል ማለት ነው።

የተባበሩት መንግስታት እንደገለጸው ሁኔታው ባስ ሲል አንዳንዴ ስደተኞቹ ከሚልኩት ገንዘብ 25 በመቶውን ለገንዘብ ተቋማቱ እንዲከፍሉ የሚገደዱባቸው ሁኔታዎች ብዙ ናቸው።

Image copyright Getty Images

ከውጪ ሃገራት የሚላከው ገንዘብ በአፍሪካና በእስያ በሚገኙ 18 ሃገራት ትምህርት ላይ የሚውለውን ወጪ በ35 በመቶ ያሳደገው ሲሆን፤ በደቡብ አሜሪካ በሚገኙ ሃገራት ደግሞ 50 በመቶ ከፍ እንዲል አድርጎታል።

ትራምፕ ውግዘት ከደረሰባት ሳዑዲ ጎን ቆመዋል

ዌል የተባለው የባህር እንስሳ 6 ኪሎ ያህል ኩባያ ውጦ ተገኘ

ፊሊፒንስ ውስጥ ከውጪ ሃገራት ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ላኩ ማለት ህጻናት ለጉልበት ስራ ከመሰማራት ተላቀው ወደ ትምህርት ቤት ይሄዳሉ ማለት ነው።

ምንም እንኳን ስደተኞች በውጪ ሃገራት ሲቀጠሩ በጣም ዝቅተኛ ክፍያ ያላቸው ስራዎችን ቢሆንም የሚያገኙት፤ ካላቸው ላይ ቆጥበው ግን ልጆቸቸውን ማስተማር እንዲሁም ቤተሰባቸውን መርዳት ግዴታቸው ይመስላል።

እነዚህ ስደተኞች ወደ ሃገራቸው የሚልኩት 8 ቢሊዮን ዶላር የእንግሊዝ መንግስት ለውጪ እርዳታ ከሚያውለው ገንዘብ ይበልጣል።

ተያያዥ ርዕሶች