ብርቱካን ሚደቅሳ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንደሚሾሙ ይጠበቃል

ብርቱካን ሚደቅሳ

የቀድሞዋ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ነገ በሕዝብ ተወካዯች ምክር ቤት ተገኝተው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን የመምራት ኃላፊነታቸውን በይፋ እንደሚረከቡ ለእርሳቸው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

የሕዝብ ተወካዯች ምክር ቤትም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ ሰብሳቢን ለመምረጥ የቀረበ የውሳኔ ሐሳብን መርምሮ ያጸድቃል።

አቶ ነብዩ ባዘዘው በ1992 ወይዘሪት ብርትኳን በግላቸው ለመወዳደር ከወሰኑበት ጊዜ ጀምሮ የምርጫ ቅስቀሳቸውን በማስተባበር፣ አስተባባሪዎችን በማሰባሰብ፣ የቅስቀሳ መድረኮችን በማመቻቸትና ከሰዎች ጋር የምትገናኝበትን ጊዜ በማመቻቸት ተሳትፈዋል።

ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ በነበረበት ጊዜ፣ ከተበተነም በኋላ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሲመሰረት በጋራ ሰርተዋል።

"በአስር ላይ ሆና፤ ከተፈታች በኋላ፤ ድጋሚ እስር ቤት ስትገባ፤ ስትወጣ፤ ውጭ ሃገር እያለችም ሆነ አሁን ስትመጣ አቀባበሏን በማሰተባበር በቅርበት ተሳትፌያለሁ"ይላሉ።

"ቀጣዩን ምርጫ ከዳር ሆኜ ባልታዘብም ተወዳዳሪ ግን አልሆንም" ብርቱካን ሚደቅሳ

"ሃገሬን ሳላስብ የዋልኩበት፤ ያደርኩበት ቀን የለም" ብርቱካን ሚደቅሳ

ሪፖርተሮቻችንም ወይዘሪት ብርትኳን ወደ አዲስ አበባ መጣችበት ጊዜ በመኖሪያ ቤታቸው በተገኙበት ጊዜ አቶ ነብዩ አቀባበላቸውንና የመገናኛ ብዙሃንን ቃለመጠይቆች ሲያስተባብሩ አግኝተዋቸው ነበር።

አቶ ነብዩ እንዳጋገጡት ወይዘሪት ብርትኳን ሚደቅሳ በእርግጥም ነገ በአትዮጵያ ፓርላማ ተገኝተው ኃላፊነቱን በይፋ ይቀበላሉ።

ቤተሰቦቻቸው፤ የትግል አጋሮቻቸውና የቅርብ ወዳጆቻቸውም በቦታው ተገኝተው መርሃግብሩን ለመከታታል እንዲችሉ መግቢያ እንደተላከላቸው ገልጸዋል።

ወይዘሪት ብርትኳን ወደ ሃገር ቤት ከተመለሱ በኋላ ከሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር በየትኛው ቦታ ተመድበው መሥራት እንደሚችሉ ከተወያዩ በኋላ የምርጫ ቦርዱን እንዲመሩ ከሥምምነት መደረሱን ነው አቶ ነብዩ ያስታወቁት።

በከፍተኛ ኃላፊነት ምርጫ ቦርድ ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራዊያዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ነጻና ገለልተኛ ተቋም ለመመስረት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ በሚችሉበት በዚህ ቦታ መስራት የሥምምነታቸው መሰረት ነው ብለዋል።

ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት ያግዛል በሚል የምርጫ ቦርድንም በአዲስ መልክ ለማዋቀር ጥናት እየተደረገ ነው።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከተለመደው የአቀባበል አጀብ ይልቅ በጥቂት ቤተሰቦቻቸውና የቅርብ ወዳጆቻቸው ብቻ የተወሰነ እንዲሆን መርጠዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ