ጀርመናዊው ታዳጊ መንጃ ፈቃድ በተሰጠው በ49 ደቂቃ ውስጥ ተነጠቀ የሚሉና ሌሎችም

Image copyright Getty Images

ኤርትራ

በኤርትራ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ የብስክሌት ውድድር 'በውስን ሰዓት' ቀድሞ በማጠናቀቅ ኤርትራ በሁለቱም ፆታ ምድብ አሸናፊ ሆናለች።

ኢትዮጵያ ደግሞ በሴቶች ምድብ ሁለተኛ ደረጃን አግኝታለች።

ሶማሊያ

የአሜሪካ መራሹ ኃይል በሶማሊያ በፈፀመው የአየር ድብደባ 37 የአልሻባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ አስታወቁ።

በድብደባው ንፁሃን ዜጎች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖር አለመኖሩ ለጊዜው ማጣራት እንዳላደረገም ጨምሮ ገልጿል።

ኬንያ

በኬንያ በአንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት የምትሰራ ጣሊያናዊት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተጠለፈች።

ታጣቂዎቹ ግለሰቧን ከመጥለፋቸው አስቀድሞ 2 ህፃናትን ጨምሮ በ5 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ወሎ በነዳጅ 'ልትባረክ' ይሆን?

ካሜሩን

በካሜሩን ከትምህርት ቤት በተቀናቃኝ ኃይሎች ከተጠለፉ ተማሪዎች መካከል 3ቱ በአገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ነፃ ወጡ።

እነሱን ለማስለቀቅ በተደረገው ግብግብም 4 ጥቃት አድራሾች የተገደሉ ሲሆን አንደኛው ሊያዝ ችሏል።

አንድ አስተማሪን ጨምሮ ዘጠኝ ተማሪዎች ኩምባ ከሚገኘው ትምህርት ቤት ተጠልፈው የተወሰዱት ትናንት ነበር።

ሊቢያ

የሊቢያ ባለስልጣናት፤ ከሰሞኑ ከአደጋ ከታደገቻቸው የእቃ መርከብ ከመውረድ ሞት ይሻለናል ያሉ ስደተኞችን በግድ እያስወረዱ መሆናቸውን አስታወቁ።

ከ90 የሚበልጡ ስደተኞችን በግድ እንዳስወረደ የተገለፀ ሲሆን እንዲወርዱ ለማድረግ አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸውን ተናግረዋል።

ዝምባብዌ

በዝምባብዌ ለረጂም ጊዜ አገሪቷን ሲመሩ የነበሩት ፕሬዚዳንት ሙጋቤ ከስልጣን የወረዱበት 1ኛ ዓመት እየተከበረ ነው።

ምክትላቸው የነበሩት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ስልጣኑን በመረከብ አገሪቱን እየመሩ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ

ኖርዌይ

በኖርዌይ የ26 ዓመቱ ወጣት በ300 ህፃናት ወንዶች ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ በመፈፀም ክስ ቀረበበት።

ግለሰቡ ራሱን ሴት በማስመሰል በስዊድን፣ ኖርዌይና ደንማርክ የሚገኙ ህፃናትን በበይነ መረብ አማካኝነት እያታለለ ላልተገባ ድርጊት ሲያነሳሳ ቆይቷል።

የመን

ባለፉት 3 ዓመታት በየመን 85 ሺ ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ሴቭዘቺልድረን አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት 14 ሚሊዮን የመናውያን ከባድ ረሃብ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ገልጾ ነበር።

85 ሺ የየመን ህጻናት በምግብ እጥረት ሞተዋል

ጀርመን

የ18 ዓመቱ ጀርመናዊ መንጃ ፍቃድ በተሰጠው በ49ኛው ደቂቃ መንጃ ፈቃዱን ተነጠቀ።

ታዳጊው በሰዓት 50 ኪሎሜትር የፍጥነት ወሰን በሚሽከረከርበት ክልል ፍጥነቱን በእጥፍ ጨምሮ 95 ኪሎ ሜትር በሰዓት ሲያሽከረክር በመያዙ ነው የተነጠቀው።

አሜሪካ

ሳዑዲ አረቢያ ከጀማል ካሾግጂ ግድያ በተያያዘ ዓለም አቀፍ ውግዘት ቢደርስባትም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ግን ከሃገሪቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሳዑዲ ተባባሪ እና ከየትኛውም ሃገር በላይ በአሜሪካ መዋለ ንዋይዋን ያፈሰሰች ናት ሲሉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች