ደቡብ ኮሪያዊው ፓስተር አማኞችን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ታሰሩ

ፓስተር ሊ ጃኢሮክ Image copyright JUNG YEON-JE

አንድ ደቡብ ኮሪያዊ ፓስተር ስምንት የቤተክርስቲያኑ አማኞችን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ተከሰው 15 ዓመት ተፈረደባቸው።

ሊ ጃኢ ሮክ የተባሉት የ75 ዓመት 'ማሚን ሴንትራል ቸርች' የተሰኘ ቤተክርስቲያን አገልጋይ 130 ሺ ተከታዮች ያሏቸው ሲሆን፤ የቀረበባቸውን ክስ አልፈጸምኩም በማለት ሲከራከሩ ነበር።

ተጎጂዎቹ ሴቶች ፓስተር ሊ ቅዱስ መንፈስ በእኔ ውስጥ አለ ስለሚሉን የታዘዝነውን ነገር ሁሉ እንፈጽም ነበር ብለዋል፤ ''አምላክ እኔ ነኝ'' ይሉም ነበር ብለዋል።

አብዛኛዎቹ ደቡብ ኮሪያውያን በትልልቅና ብዙ ገንዘብ እንዲሁም ተጽዕኖ መፍጠር በሚችሉ ቤተክርስቲያኖች ውስጥ ይጠቃለላሉ። ነገር ግን እዚም እዚያም ከዋናዎቹ ቤተክርሰቲያኖች ተገንጥለው የራሳቸውን አገልግሎት የሚሰጡ ቤተክርስቲያኖችም አሉ።

የቦርዱ ማሻሻያና የብርቱካን ሹመት ምንና ምን ናቸው?

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ

አብዛኛዎቹ ተገንጣይ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ በማጭበርበርና ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ ያተኮሩ ናቸው።

የፓስተር ሊ ቤተክርስቲያንም ከእነዚህ መካከል አንዱ ነው ተብሏል።

ቤተክርስቲያኑ እ.አ.አ በ1982 ሲሆን የተቋቋመው፤ በመጀመሪያ 12 አባላት ብቻ ነበሩት። በአሁኑ ሰአት ግን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ሲሆን፤ የራሱ ዋና መስሪያ ቤትና ታዋቂ የበይነ መረብ ፈውስ አገልግሎት መስጫም አለው።

አነጋጋሪው የአስገድዶ መድፈር ጉዳይ ለህዝብ ጆሮ መድረስ የጀመረው ባለፈው ዓመት አንዳንድ ሴቶች ፓስተሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመጡ እየጠየቁ ግብረ ስጋ ግንኙነት ከእሳቸው ጋር ካልፈጸሙ እንደማይፈወሱ እንደተነገራቸው ይፋ ሲያደርጉ ነው።

''እሳቸውን እምቢ ማለት ከባድ ነው። እሳቸው ማለት ንጉስ ናቸው። እንደ አምላክም ናቸው። ከልጅነቴ ጀምሮ የቤተክርስያኑ ተከታይ ነበርኩ'' ብላለች አንዲት ሴት።

ተመሳሳይ ጥቃት ደርሶብናል ያሉ ስምንት ሴቶች ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቀረቡ። ባለፈው ግንቦት ወር ላይም ፓስተሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ወሎ በነዳጅ 'ልትባረክ' ይሆን?

የፍርድ ውሳኔው በዋናው ዳኛ ሲነበብ ፓስተር ሊ አይናቸውን ጨፍነው ነበር ተብሏል።

እስከ መጨረሻው ውሳኔ ድረስም ሴቶቹ ያልተገባ ባህሪ በማሳየታቸው ከቤተክርስቲያኑ የተወገዱ ናቸው በማለት ሲከራከሩ ነበር፤ ፓስተሩ።