ትራምፕ ከሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ጋር እሰጥ አገባ ገጥመዋል

ትራምፕ ከሃገሪቱ ከፍተኛ ዳኛ ጋር እሰጥ አገባ ገጥመዋል Image copyright Getty Images

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ «የኦባማ ዳኛ» በሚል በሰጡት አስተያየት ምክንያት ከሃገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋር ተቃቅረዋል።

የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ጆን ሮበርትስ ትራምፕ አንድ ዳኛን በተመለከተ የሰጡ አስተያየት ተገቢ አይደለም በሚል ነው ቅር የተሰኙት።

ባለፈው ማክሰኞ ነበር አንድ የፌዴራል ዳኛ የትራምፕን የስደተኞች ፖሊሲ ውድቅ ያደረጉት፤ ይህን ተከትሎም ትራምፕ ዳኛው «የኦባማ ዳኛ» በሚል ወረፈዋቸዋል።

ትራምፕ ለሰሜን ኮሪያ፡ "እንዳትሞክሩን"

አስተያየቱ ያልጣማቸው ዳኛ ጆን ሮበርትስ «ዳኛዎቻችን የኦባማም አይደሉም፤ የትራምፕ፣ የክሊንተን ወይ የቡሽ አይደሉም» ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

«ያሉን ዳኞች እጅግ የተማሩ እና ፍትህን ለሚሹ ፍትህ ለመስጠት የሚታትሩ ናቸው» በማለት ሃሳባቸውን አስረግጠዋል።

ትራምፕ መንበረ ሠልጣኑን ከጨበጡ ወዲህ ከከፍተኛው ፍርድ ቤት አንዲህ ዓይነት ተቃውሞ ገጥሟቸው አያውቅም።

ሜላኒያ ትራምፕ የትራምፕን ፖሊሲ ተቃወሙ

የምስጋና ቀን በሚል አሜሪካኖች በሚያከብሩት በዓል ዋዜማ ላይ የተገኙት ትራምፕ ከምስጋና ይልቅ ትችት ከአፋቸው አልተለየም።

«የኦባማ ዳኞች ሃገራችንን ለመጠበቅ ሌተቀን ደፋ ቀና ከምንል ሰዎች ጋር ሰፊ የሆነ የሃሳብ ልዩነት ነው ያለን» በማለት ነው ዳኞቹን በነገር ወጋ ያደረጉት።

ከኛ በላይ ዴሞክራሲ. . .የምትለው አሜሪካ ፌዴራል ዳኛዋ እና ፕሬዝደንቷ መሰል ቅራኔ ውስጤ ሲገቡባት ማየት ዘበት ነው፤ ዕድሜ ለትራምፕ ሁኔታውን ወደነበር ቀይረውታል።

ትራምፕ ውግዘት ከደረሰባት ሳዑዲ ጎን ቆመዋል