የጓቲማላ የቀድሞ ወታደር 5,160 ዓመታት እስር ተበየነባቸው የሚሉና ሌሎችም

አፍሪካ

በአፍሪካ የህፃናት ጋብቻ በትንሹ 63 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንዳስከተለ ዓለም ባንክ አስታወቀ።

ጥናቱ በአፍሪካ 12 አገራት የተካሄደ ሲሆን ህፃናቱ በጋብቻ ምክንያት ትምህርታቸውን ስለሚያቋርጡ የኋላ ኋላ የሚያስገኙት ገቢ አነስተኛ በመሆኑ ነው ኪሳራው ያጋጠመው።

ቱኒዚያ

በቱኒዚያ 650 ሺህ የመንግስት ሰራተኞች 'ደመወዛችን አነሰን' ሲሉ አድማ መቱ።

በሺዎች የሚቆጠሩም አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ይሁን እንጂ መንግስት በዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ቁጥጥር ፈንድ (አይ ኤም ኤፍ) የኢኮኖሚ ቀውሱን ለማስተካከል ጫና ስለተደረገብኝ ጭማሬ አላደርግም ብሏል።

አድማው በ5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነው።

የአየር ንብረት ለውጥ

የዓለም የሙቀት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የዓለም ሜትዮሮሎጂ ድርጅት አሳሰበ።

ይህም ኢንዱስትሪ ከመስፋፋቱ አስቀድሞ ካለው ጋር ሲነፃፀር 146 በመቶ መጨመሩ ተመልክቷል።

ላቲቪያ

በላቲቪያ የህንፃ መስታወቶችን የምታፀዳና እሳትን የምታጠፋ ሰው አልባ አውሮፕላን ተፈበረከች።

55 ኪሎ ግራም የምትመዝነው ሰው አልባ አውሮፕላን ከሰው በ20 እጥፍ ፈጣን ስትሆን የእሳት አደጋ መሰላሎች የማይደርሱበትም ትደርሳለች።

ያለአብራሪ በሚበረው የሰማይ ታክሲ ይጠቀማሉ?

አውስትራሊያ

በአውስትራሊያ ደቡብ ምስራቃዊ ግዛት የተከሰተው የአቧራ ብናኝ የአየር ብክለት አስከተለ።

500 ኪሎሜትር በሸፈነው አቧራ ሳቢያ ሰዎች ወደ ግዛቲቱ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለ ሲሆን በረራዎችም ተስተጓጉለዋል።።

ጓቲማላ

የጓቲማላ የቀድሞ ወታደር 5,160 ዓመታት እስር ተበየነባቸው።

በጓቲማላ 'ዶስ እርስ' በተባለች መንደር ከ36 ዓመታት በፊት በተፈፀመ ጭፍጨፋ ከ200 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፤ የቀድሞው ወታደር ሳንቶስ ሎፔዝ በ171 ሰዎች ግድያ ጥፋተኛ ተብለዋል።

ወታደሩ በአንድ ሰው ግድያ 30 ዓመት የተፈረደባቸው ሲሆን በህይወት የተረፈችን ታዳጊ በመግደላቸው ሌላ ተጨማሪ 30 ዓመት ተከናንበዋል።

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ: ‘‘ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም፤ ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው’’

ጣሊያን

በጣሊያን በመካከለኛው ዘመን ዘመም ተደርጎ የተገነባው የመታሰቢያ ሐውልት ቀና ቀና እያለ መሆኑ ተዘገበ።

57 ሜትር ርዝመት ያለው ሐውልት ከቀድሞ ይዞታው በ4 ሴንቲ ሜትር ልዩነት እንዳሳየ ተገልጿል።

ደቡብ ኮሪያ

ደቡብ ኮሪያዊ ፓስተር 8 የቤተክርስቲያኑ አማኞችን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ተከሰው 15 ዓመት ተፈረደባቸው።

130 ሺ ተከታዮች ያሏቸው ሊ ጃኢ ሮክ የተባሉት የ75 ዓመት ፓስተር ግን የቀረበባቸውን ክስ አልፈጸምኩም ሲሉ ተቃውመውታል።

ደቡብ ኮሪያዊው ፓስተር በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ታሰሩ

እንግሊዝ

በእንግሊዝ ከአራት ወጣት ሴቶች አንዷ ለአዕምሮ ህመም እንደምትጋለጥ የኤን. ኤች. ኤስ የበይነ መረብ ሪፖርት አስታወቀ።

ሪፖርቱ እንደጠቀሰው ከ17-19 ዕድሜ ክልል ያሉ ሴቶች ከወንዶቹ ጋር ሲነፃፀር ለህመሙ የመጋለጣቸው ዕድል በዕጥፍ ይበልጣል።

ፊሊፒንስ

በፊሊፒንስ የ23 ዓመቱ ወጣት በ4 ሰዓታት ከቀርቀሃ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ 50 ሺህ ዮሮ ተሸለመ።

ወጣቱ ኤርል ፓትሪክ ቁሳቁሶቹን ለማዘጋጀት አንድ ሳምንት የፈጀበት ሲሆን በአገሪቱ ያለው የቤት እጥረት እንዳነሳሳው ተናግሯል።

ቀርቀሃ በፊሊፒንስ በቀላሉ የሚበቅል ተክል ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ