ሞሮኳዊቷ ፍቅረኛዋን ከምግብ ጋር ቀላቅላ በማብሰል ተከሰሰች

ሞሮኳዊቷ ፍቅረኛዋን ገድላ በማብሰል ተከሳሰች Image copyright Alamy
አጭር የምስል መግለጫ ሞሮኳዊቷ ፍቅረኛዋን ገድላ በማብሰል ተከሳሰች

በዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ የምትኖር አንዲት ሞሮኳዊት ፍቅረኛዋን ገድላ፣ የሰውነት ክፍሉን ከምግብ ጋር ቀላቅላ በማብሰሏ ተከሳለች። 'ዘ ናሽናል' ጋዜጣ እንደዘገበው፤ ሞሮኳዊቷ የፍቅረኛዋን የሰውነት ክፎሎች ከምግብ ጋር ቀላቅላ አብስላ ለፓኪስታናውያን መመገቧም በክሱ ተጠቅሷል።

ሬሳን ከሞት አስነሳለሁ ያለው 'ነብይ' የሟች ቤተሰብን እንዴት አሳመነ?

ደቡብ ኮሪያ ትልቁን የውሻ 'ቄራ' ዘጋች

ትራምፕ ከሃገሪቱ ከፍተኛ ዳኛ ጋር እሰጥ አገባ ገጥመዋል

የዱባዩ 'ገልፍ ኒውስ' እንደዘገበው፤ ሞሮኳዊቷ ከፍቅረኛዋ ጋር ሰባት ዓመታት አሳልፋለች። ሆኖም ሞሮኮ ውስጥ ከሌላ ሴት ጋር ትዳር ሊመሰርት መሆኑን ሲነግራት እንደገደለችው ተዘግቧል።

በ30ዎቹ እድሜ ክልል የምትገኘው ሞሮኳዊት፤ ፍቅረኛዋን የገደለችው ከሦስት ወራት በፊት ነበር ተብሏል። ግድያውን ከፈጸመች በኋላ ከጓደኛዋ ጋር በመተባበር ቤቷን እንዳጸዱም ተገልጿል።

ከዛም ለፍቅረኛዋ ወንድም ፍቅረኛዋን ከቤት እንዳባረረችው ተናግራለች ተብሏል። ከሦስት ወራት በፊት የፍቅረኛዋ ወንድም፤ ቤቷ አቅንቶ በቤቷ በሚገኝ የፍራፍሬ መፍጫ ውስጥ የሰው ጥርስ ሲያገኝ ለፖሊስ ማሳወቁም ተነግሯል።

ፖሊሶች የዘረ መል (ዲኤንኤ) ምርምራ ካካሄዱ በኋላ ጥርሱ የሟች መሆኑን ማረጋገጣቸው ተገልጿል።

ሞሮኳዊቷ ፍቅረኛዋን የገደለችው ማገናዘብን በሚያሳጣ ቅጽበታዊ የሆነ አዕምሮን መሳት (ቴምፖራሪ ኢንሳኒቲ) ምክንያት እንደሆነ የእምነት ክህደት ቃሏን ሰጥታለች።

ፖሊስ ምርመራውን ካጠናቀቀ በኋላ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የሚቀርብ ይሆናል። የተጠርጣሪዋን አዕምሮ ጤንነት ለማረጋገጥ ወደ ሆስፒታል መወሰዷም ተነግሯል።

ፖሊሶች ሞሮኳዊቷ ፍቅረኛዋን እንዴት እንደገደለችው ባይናገሩም፤ የሰውነት ክፍሎቹን ከሩዝና ከሥጋ ጋር (በአካባቢው የተለመደ ባህላዊ የምግብ አሠራር) በማደባለቅ በአቅራቢያዋ ይሠሩ ለነበሩ ፓኪስታናዊ ሠራተኞች አብልታለች ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች