የአፍሪካ ፎቶዎች - ከመቐለ፣ አቢጃን፣ ካይሮ፣ ናይሮቢ

በዚህ ሳምንት አፍሪካን እና በተለያዩ የዓለም ሃገራት የሚገኙ አፍሪካዊያንን የሚያሳዩ ፎቶዎች ስብስብ።

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ በሞሮኮዋ ሳሌ ከተማ የሚገኙ ሙስሊሞች ሰኞ የመውሊድ በዓልን አክብረዋል።

ቤንጋዚ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በተመሳሳይ በሊቢያዋ ቤንጋዚ የሚገኙ ህጻናት ምሽት ላይ ክብረ በዓሉን ተቀላቅለዋል።

ካይሮ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በካይሮ ደግሞ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ተለያዩ ዕቃዎች ለሽያጭ ቀርበዋል።

ኪንሻሳ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በሚቀጥለው ወር ከሚደረገው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምርጫ በፊት ሚደረገው የምረጡኝ ቅስቀሳ ተጀምሯል። ባለፈው ረቡዕ ተቃዋሚ ፓርቲው ደጋፊዎች በርዕሰ መዲናዋ ኪንሻሳ ለድጋፍ ወጥተዋል።

ናይሮቢ

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ናይሮቢ ኬንያ የሚገኙ አካል ጉዳተኛ ተሽከርካሪ ወንበር ቦክሰኞች ልምምዳቸውን ሲያደርጉ።

እዚያው ናይሮቢ

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ልምምዱ እርስ በእርስ ቡጢ መወራወርንም ያካተተ ነው።

ካሳቭላንካ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ሞሮኮ እና ካሜሮን ካሳብላንካ ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተጫውተው ነበር። እነዚህ ደጋፊዎችም በስታዲም ተገኝተው ቡድናቸው ደግፈዋል።

ባማኮ

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ባለፈው ግንቦት ለባዕድ አምልኮ ሲባል ተገደለችውንና አልቢኖ ያለባትን የ13 ዓመቷን ራማታ ዲያራን ለማሰብ በተዘጋጀው ኮንሰርት ላይ ሳሊፍ ኪዬታ ሙዚቃውን አቅርቧል።
Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ዝግጅቱን ለመታደም አልቢኖዎች በብዛት ተገኝተዋል።

አቢጃን

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በአይቮሪኮስት ዋና ከተማ አቢጃን ነጋዴዎች ለገበያ ያቀረቧቸው ባለተለያየ ቀለም ጀሪካኖች።

መቐሌ

Image copyright Girmay Gebru
አጭር የምስል መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ በምትገኘው መቐሌ አንድ ነጋዴ ለሽያጭ ያዘጋጃቸውን አምስት ዶሮዎች ይዞ ወደ ገበያ ወጥቷል።

የፎቶ ምንጮች AFP፣ EPA፣ Reuters እና Getty Images nacwe.

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ

ተያያዥ ርዕሶች