የአፍሪካ ኅብረት ሴት ሠራተኞች ወሲባዊ ትንኮሳ እንደሚፈፀምባቸው ጥናት አመለከተ የሚሉና ሌሎችም

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጥቃት አድራሾቹ ላይ ርምጃ ለመውሰድ ቃል ገብቷል

ኢትዮጵያ

ትናንት የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ግድያ ለማውገዝ በወጡ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተወካይ ወ/ሮ ይዳኝ ማንደፍሮ ለቢቢሲ እንደገለፁት በግጭቱ 12 ተማሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

ከእነዚህ መካከል 10 ተማሪዎች አስፈላጊው ሕክምና አግኝተው ወዲያው የተመለሱ ሲሆን 2 ደግሞ ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ችግሩን ለመፍታትም ከተማሪ ተወካዮች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ብለዋል።

***

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ ባለፈው ረቡዕ በተፈፀመ ጥቃት የሰው ሕይወት ጠፋ።

የክልሉ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሳ አሕመድ በጥቃቱ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ገልፀዋል።

ጥቃቱ በታጠቂዎች የደረሰ ሲሆን አሁንም በከተማዋ ውጥረት እንዳለ ተናግረዋል።

"የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ

"ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

በዲሞክራቲክ ኮንጎ በርካታ ሕጻናት በኢቦላ ቫይረስ መያዛቸው የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

በዚህ ሳምንት ብቻ 36 ተጠርጣሪ ህሙማን የተገኙ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 7 ቱ ጨቅላ ሕጻናት ናቸው።

አፍሪካ

የአፍሪካ ኅብረት ሴት ሠራተኞች ወሲባዊ ትንኮሳ እንደሚፈፀምባቸው አንድ የውስጥ ጥናት አስታወቀ።

አብዛኞቹ ተጠቂዎች ጊዜያዊ ሠራተኞች፣ ወጣት በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም በሥራ ልምምድ ላይ የሚገኙ እንደሆኑ በጥናቱ ተጠቅሷል።

አውስትራሊያ

በአውስትራሊያ የሰደድ እሳትን ለመቆጣጠር ቦይንግ 737 አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ ሥራ ላይ ዋለ።

አውሮፕላኑ ከ15 ሺህ ሊትር በላይ ውሃ የሚይዝ ሲሆን 63 የእሳት አደጋ ሠራተኞችንም ማሳፈር እንደሚችል ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።

"ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ

እንግሊዝ

እንግሊዝ የሴት ልጅ ግርዛትን በአፍሪካ ለማስቀረት 64 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ልታደርግ ነው።

የአገሪቱ መንግሥት እንዳስታወቀው ይህንን ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው በአውሮፓውያኑ 2030 የሴት ልጅ ግርዛትን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት አልሞ ነው።

አሜሪካ

በካሊፎርኒያ ግዛት የተነሳው የሰደድ እሳት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአካባቢው ባሥልጣናት አስታወቁ።

83 ሰዎች የሞቱበትና ከ500 በላይ የጠፉበት የሰደድ እሳት በዝናብ አማካኝነት የጠፋ ቢሆንም የመሬት መንሸራተት ግን ስጋት መሆኑ አልቀረም።

ብራዚል

በብራዚል በጫካ ውስጥ የተገነባው አዳሪ ት/ቤት ለዓለማችን ምርጥ ሕንጻዎች የሚሰጠውን 'ሪባ' የተሰኘ ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኘ።

ለ540 ረዳት ለሌላቸው ተማሪዎች ማደሪያ የተገነባው ይህ ሕንፃ በሚያምር መልኩ በእንጨት የተሠራ ነው።

ደቡብ ኮሪያ

ሳምሰንግ በፋብሪካው ውስጥ በሥራ ላይ እያሉ ለህመምና ለሞት የተዳረጉ ሠራተኞችን በይፋ ይቅርታ ጠየቀ።

ድርጅቱ በዚህ ወር መጀመሪያ በሥራው ምክንያት ለሚታመሙና ለሚሞቱ ሰዎች ካሳ ለመክፈል የተስማማ ቢሆንም ይቅርታውን የጠየቀው ግን ልጃቸው በደም ካንሰር የሞተችባቸው አባት ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ ነው።

***

ደቡብ ኮሪያ በሃገሪቱ ትልቁ የሚባለውን የውሻዎች ማረጃና ማቀነባበሪያ ማዕከል ማፈራረስ ጀመረች።

ታዪፒዮንግ ዶንግ የተባለው ይህ እጅግ ሰፊ የሆነ ማዕከል በቅርቡ ለከተማዋ ነዋሪዎች የመዝናኛ ማዕከል ይገነባበታል ተብሏል።

ደቡብ ኮሪያ ትልቁን የውሻ 'ቄራ' ዘጋች