የቀድሞ የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ መራመድ ተስኗቸዋል

ሮበርት ሙጋቤ Image copyright Reuters

የ94 ዓመቱ አዛውንት ሮበርት ሙጋቤ የጤናቸው ሁኔታ እያደር እየባሰ በመሄዱ ምክንያት መራመድ እንደተሳናቸው ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ተናገሩ።

ምናንጋግዋ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምናቸውን እንዳመማቸው ግልፅ ባይደረግም ላለፉት ሁለት ወራት በሲንጋፖር ህክምና እየተከታተሉ እንደሆነ ተናግረዋል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት በስልጣን ላይ እያሉ ጭምርም ወደ ሲንጋፖር ለህክምና ይመላለሱ ነበር።

ምናንጋግዋ ከአመት በፊት ነው በወታደሩ ጣልቃ ገብነት የፕሬዝዳንትነት መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት።

"የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ

"ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ

የሮበርት ሙጋቤ ጥቅሶች

ሙጋቤ በመሪነት ስልጣኑ ላይ ለ37 ዓመት የነበሩ ሲሆን መጀመሪያ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቀጥሎም በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል።

ዚምባብዌን ከነጮች አገዛዝ ነፃ ለማውጣት የነበረውን ትግልም መርተዋል።

ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ በሮበርት ሙጋቤ የትውልድ ስፍራ አካባቢ ለተሰበሰበ ህዝብ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው የጤንነታቸውን ሁኔታ የተናገሩት።

"አርጅተዋል። መራመድ አቅቷቸዋል ነገር ግን የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ከማድረግ ወደኋላ አንልም" ማለታቸውን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ለመራመድ ከመቸገራቸው ውጪ የጤንነታቸው ሁኔታ በመሻሻሉ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱም አክለው ገልፀዋል።

እንደ ፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘገባ ከሆነ ምናንጋግዋ በንግግራቸው "እየተንከባከብናቸው ነው፤ የዚምባብዌ መስራች ናቸው፤ የነፃዋ ዚምባብዌ መስራች ከሆኑት መካከል ናቸው" ብለዋል።

የሙጋቤን የህክምና ወጪ መንግሥት እንደሚሸፍን ማወቅ ተችሏል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ