የጋና ቅንጡ የሬሳ ሳጥኖች-ፍልስስ እያሉ ወደ መቃብር መሄድ

የመኪና ሬሳ ሳጥን 65032 Image copyright Fellipe Abreu

ጋናዊያን አይደለም የቆመን የሞተን ለማስደሰት የሚተጉ ናቸው። የሬሳ ሳጥን ሲሰሩ ሰው በህይወቱ ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን ህልም፣ ምኞት፣ እና የኑሮ ደረጃ ያገናዘበ ነው።

ይህንን ሀሳባቸውን የሚደግፉላቸው ደግሞ የሟች ቤተሰቦች ናቸው። የሟች ቤተሰቦች የሟችን የመጨረሻ ጉዞ ለማሳመር ይፈልጋሉ።ታዲያ ይህ የመጨረሻ ስንብት ምርጥ ሽኝት እንዲሆን ማድረግ የቀብር አስፈፃሚ ድርጅቶችም ስራ ነው።

"ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ

"የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ

Image copyright Fellipe Abreu

ጋና ካካዋ በማምረት በአለማችን ቀዳሚ ከሆኑት ሀገራት መካከል አንዷነች። ታዲያ በጋና ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ጋናውያን ጥረው ግረው የቋጠሯትን ጥሪት ሟች ዘመዳቸውን በካካዋ አምሳል በተሰራ ሬሳ ሳጥን ለመቅበር ይከፍላሉ።

ይህን አይነቱ የሬሳ ሳጥን 28ሺህ ብር ድረስ ያስወጣል። ታዲያ አብዛኛው ከእጅ ወዳፍ የሆነ ኑሮ የሚገፋው ጋናዊ ገበሬ የቀን ገቢው በቀን 80 ብር ገደማ ነው።

Image copyright Fellipe Abreu

የሬሳ ሳጥን ሲዘጋጅ የሟችን ሥራ ያገናዘበ ነበር። በዚህኛው የሬሳ ሳጥን ግን "በቃሪያ ቅርፅ የተሰራው ከገበሬው ህይወት ባሻገር ትርጉም አለው "ይላል ላለፉት 50 አመታት እንዲህ የሬሳ ሳጥን በማበጃጀት ስራ ላይ የተሰማራው አናጢው ኤሪክ አጄቲ።

የቃሪያው መቅላት እና ቅመምነት የሰውየውን ሰብዕና ይወክላል። "ቁጡና ሀይለኛ ነበር፣ ማንም ቢሆን ከእርሱ ጋር መጋጨት አይፈልግም።"

Image copyright Fellipe Abreu

እንዲህ በሜርሴዲስ ቤንዝ የተመሰሉ የሬሳ ሳጥኖች ዝነኞች ናቸው። ይህ ሟች ሐብታምና ጀርመን ሰራሹን ሜርሴዲስ ያሽከረክር እንደነበር ያሳያል። አሁንም የመቃብር ጉድጓዱ መኪናውን ማስገባት በሚችል መልኩ ተቆፍሯል።

"ይህ ከሚዘወተሩ የሬሳ ሳጥኖች መካከል አንዱ ነው። በሐብት ጭምልቅ ያለ እንደነበር ይናገራል" ይላል የሬሳ ሳጥን ሰራተኛው ስቲቭ አንሳህ።

በርካታ ሰዎች ቅንጡ የሬሳ ሳጥኖች ብለው ይጠሯቸዋል፤ የሀገሬው ሰው ግን 'አቤዱ አዴኪ' ወይንም "የተምሳሌት ሳጥን" ይላቸዋል።

ለዚህ ደግሞ ሰበቡ ከእያንዳንዱ ሳጥን ጀርባ ተምሳሌት የሆነ ነገር ስላለ ነው።

Image copyright Fellipe Abreu

አውሮፕላን ከዝነኛ የሬሳ ሳጥኖች መካከል አንዱ ነው። ይህ የተሰራው ለህፃን ልጅ ሲሆን ከሞት ባሻገር ባለው ህይወት መልካም ጉዞ እንዲገጥመው ተምሳሌት የሚያደርግ ነው።

አንዳንዴ የአካባቢው ሰዎች የሬሳ ሳጥኑን ለመግዛት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለመሸፈን ያላቸውን ያዋጣሉ።

Image copyright Fellipe Abreu

ከቅርብ አመታት ወዲህ የቤት ግንባታ በጋና ተጧጡፏል። ታዲያ ይህ የሬሳ ሳጥን ቤት እየሰራ የሚያከራይና በአካባቢው ማህበረሰብ ተወዳጅ ለሆነ ግለሰብ የተዘጋጀ ነው።

"የሬሳ ሳጥን መግዛት የሟች ቤተሰብ ኃላፊነት ነው፤ ለቀብር ማስፈፀሚያ መክፈል፣ ለሟች ልብስ መግዛት እንዲሁም ለለቀስተኞች መሸኛ ምግብና መጠጥ ማቅረብም የቤተሰቡ ወጪ ነው።"

"ቀብር የሚፈፀመው ከሐሙስ እስከ ሰኞ ባሉት ቀናት ነው። ሐሙስ ዕለት የሬሳ ሳጥን ይገዛል፣ አርብ ዕለት ሬሳው ካለበት ሆስፒታል ይመጣል፣ ቅዳሜ ቀብሩ ይካሄዳል፤ እሁድ ዕለት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል። ሰኞ ለቅሶ ለመድረስ ከመጡ ሰዎች የተሰበሰበውን ገንዘብ የመቁጠሪያ ቀን ነው" ይላል አጄቴ።

Image copyright Fellipe Abreu

አናጢው እንዲህ አበጃጅቶ የሰራውን የሬሳ ሳጥን በአግባቡ ጠርቦ ልጎ ለመቀባት ዝግጁ ያደርገዋል። አሁን ይህን የድምፅ ማጉያ ቅርፅ ያለውን የሬሳ ሳጥን ድምፃዊ ሲሞት የሚቀበርበት ነው።

"ሟች የሬሳ ሳጥኑ ይብቃው፣ ይሁን አይሁን የምናውቀው ነገር የለም፤ አንዳንዴ ቤተሰብ እንጠይቃለን ካልሆነም ፎቶ እናያለን" ይላል አናጢው አንሳህ።

Image copyright Fellipe Abreu

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሌሎች አናጢዎችም የገበያውን ፍላጎት ለሟሟላት በማሰብ የተለያዩ ቅርፆች ያሏቸውን ሳጥኖች መስራት ጀምረዋል።

Image copyright Fellipe Abreu

ይህ የሬሳ ሳጥን አይደለም፤ አሜሪካ ፍላደልፊያ ለሚገኝ የጥበብ ማዕከል የተሰራ ነው። ባለፉት አስርት አመታት ከ20 ሀገራት በላይ እነዚህን የሬሳ ሳጥኖች ገዝተዋቸዋል።

የሬሳ ሳጥኖቹ ቅርፅ በደቡብ ኮሪያ፣ ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ዴንማርክ የእንጨት ስራ የሆኑ ተማሪዎችን ትኩረት በመሳቡ ጋና ድረስ መጥተዋል።

እነዚህ ጋናውያን አናጢዎች ግን የሬሳ ሳጥኑን ለማበጃጀት እና መልክ ለመስጠት የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች በአካባቢው የሚገኙ ቀላል መሳሪያዎችን ነው።

Image copyright Fellipe Abreu

ተያያዥ ርዕሶች