ናይጀሪያ ኤኒና ሼል ባደረጉት የተጭበረበረ የነዳጅ ስምምነት 6 ቢሊዮን ዶላር ከነዳጅ አጣች

የነዳጅ Image copyright Getty Images

በጣሊያኗ ከተማ ሚላን የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት በነዳጅ አምራች ኩባንያዎቹ ኤኒኒና ሼል ክስ ለመክፈት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ሁለቱ ኩባንያዎች ከናይጀሪያ ጋር ባደረጉት የተጭበረበረና ሙስና የተሞላበት የነዳጅ ስምምነት ምክንያት ሀገሪቷን 6 ቢሊዮን ዶላር በማሳጣታቸው ምክንያት ነው።

በናይጀሪያ እየተካሄደ ያለውን የተጭበረበረ ስምምነት ላይ ዘመቻ እያካሄደ ያለው ግሎባል ዊትነስ የተባለው ድርጅት በአውሮፓውያኑ 2011 የተደረገው ኦፒኤል የተባለው የነዳጅ ስምምነት የሀገሪቱን አመታዊ የትምህርትና የጤና እጥፍ በጀት እያሳጣት እንደሆነ አስታውቋል።

የሜቴክ ሰራተኞች እስር ብሔር ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ ተገለፀ

ወ/ሪት ብርቱካን በወዳጆቻቸው አንደበት

በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተ እስራኤላውያን ወደ ፅዮን ውሰዱን ተማፅኖ

የጣልያኑ ኤኒና የእንግሊዝና ሆላንድ ንብረት የሆነው ሼልም የከፈሉት ገንዘብ ለጉቦ እንዲሆን ነው በሚልም ተወንጅለዋል።

ኩባንያዎቹ ምንም አይነት ስህተት አልሰራንም በሚል የሆነውን ሁሉ ክደዋል።

በጣልያን ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ ላይ የእንግሊዙ የደህንነት ድርጅት ኤም አይ 6 የቀድሞ አባላት፣ ኤፍ ቢ አይ፣ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የሁለቱ የነዳጅ ኩባንያ ስራ አስፈፃሚዎች በዚህ ሙስናና ማጭበርበር ላይ እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

የቀድሞው የናይጀሪያ የነዳጅ ሚኒስትር ዳን እቴቴ ፈረንሳይ በሚገኝ ፍርድ ቤት ጀልባና ቪላ ቤት ለመግዛት በሚል ገንዘብ በህገ-ወጥ በማዘዋወር ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

ፍርድ ቤቱ ጨምሮ እንደገለፀው አምስት ሺ ኪሎግራም የሚመዝን የመቶ ዶላር የብር ኖቶች ይዘው ነበር ብሏል።

ግሎባል ዊትነስ ለአመታት የዘለቀው ምርምሩ እንደሚያሳየው ሼልና ኤኒ በኒጀር ዴልታ አካባቢ የነዳጅ ቁፋሮን መብት አግኝተው እንደነበር ነው።

በኩባንያዎቹና በናይጀሪያ የተደረገው ስምምነት ኩባንያዎቹን ሆን ብሎ እንዲጠቅም የተደረገ ሲሆን በዚሀም ምክንያት ናይጀሪያ 5.86 ቢሊዮን ዶላር እንዳጣች ተገልጿል። ይህም ስምምነቱ ከተፈረመ ከአውሮፓውያኑ 2011 በኋላ ያለውን ነው።

ናይጀሪያ ያጣችው ገንዘብም የታሰበው 70 ዶላር በበርሜል ተባዝቶ ነው ።

ኤኒ የተባለው ኩባንያ ሂሳቡ የተሰራበትን መንገድ የተቸ ሲሆን፤ ናይጀሪያ ስምምነቱን የመከለስ መብት እንዲሁም ከነዳጅ ገቢው 50% መጠየቋን ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንደሆነ ተገልጿል።