ከአንድ ወር በላይ የፈጀው የቼዝ ጨዋታና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

Image copyright EPA

ኢትዮጵያ

በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በዛሬው ዕለት ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ፖሊስ በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ የፖሊስ አባላት እንዲሁም ቀሪዎቹ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አጠቃላይ 33 ተጠርጣሪዎች ፈጽመዋል ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊት አቅርቧል።

***

ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የአፍሪካ የሳይክል ዋንጫ ውድድር አዘጋጇ ኤርትራ በ10 ወርቅ 6 ብርና 5 ነሃስ አንደኛ ሆና ጨረሰች።

ኢትዮጵያ በ1 ወርቅ፣ 5 ብርና 4 ነሃስ ሶስተኛ ስትሆን ደቡብ አፍሪካ ደግሞ በሁለተኝነት ጨርሳለች።

"ነጭ የለበሰ 'መልአክ' በኦሮምኛ አናገረኝ"- የሬሳ ሳጥን ፈንቅለው የወጡት ግለሰብ

እውን እንጀራ ሱስ ያስይዛል?

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አመፅን በፎቶ

ናይጄሪያ

ናይጄሪያ ከሙስናዊ ስምምነት ጋር በተያያዘ ከነዳጅ ንግድ ብቻ 162 ቢሊዮን ብር ማጣቷ ተገለጸ።

ከዚህ ጋር በተገናኘም የጣልያኑ ነዳጅ አምራች ኩባንያ ኤኒና የእንግሊዝና ሆላንድ ንብረት የሆነው ሼል ላይ ክስ ቀርቧል።

ደቡብ አፍሪካ

በደቡብ አፍሪካዋ ደርባን ከተማ የሚገኝ ግለሰብ ከአንድ ህንጻ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ወድቆ ህይወቱ ተረፈች።

የ47 ዓመቱ ሰው በአደጋው ከፍተኛ ጉዳት ቢድርበትም ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ክትትል እየተደረገለት ነው።

ኬንያ

የኬንያን የትምህርት ስርዓትና የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሩን የተሳደቡ ስምንት የሁለተኛ ደረጃ ያጠናቀቁ ተማሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተማሪዎቹ በማህበራዊ ሚዲያዎች የለቀቁት ተንቀሳቃሽ ምስል ሲሳደቡና በፈተናው ሲኮርጁ እንደነበረ ሲናገሩ ያሳያል።

ዴሞክራቲክ ኮንጎ

አሜሪካ በዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚገኘውን ኤምባሲዋን ከሽብር ጥቃት ጋር በተያያዘ ዘጋች።

የኤምባሲው ውሳኔ በኮንጎ ከሚካሄደው ምርጫ በፊት ሽብርን ለመንዛት የተደረገ ነው ሲሉ የሃገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ፖሊ ሙዛይላ ተናግረዋል።

ዚምባብዌ

የ94 ዓመቱ የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ መራመድ እንደተሳናቸው ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ተናገሩ።

ሮበርት ሙጋቤ ምናቸውን እንዳመማቸው ግልፅ ባያደረጉም ላለፉት ሁለት ወራት በሲንጋፖር ህክምና እየተከታተሉ እንደነበረ ገልጸዋል።

ኮሪያ

ሁለቱ ኮሪያዎች በጋራ የነጻ ትግል ውድድርን በዩኔስኮ ቅርስነት አስመዘገቡ።

ሁለቱም ሃገራት ከዚህ በፊት ለየብቻቸው ሲጠይቁ የነበረ ሲሆን፤ በጥምረት ያቀረቡት ጥያቄ ግን በዩኔስኮ ተቀባይነት አግኝቷል።

ህንድ

ህንዳዊው ወጣት አውሮፕላን ውስጥ የተነሳው ፎቶ ላይ አሸባሪ የሚል ቃል ሲጽፍ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ወጣቱ ምስሉን ለጓደኛው ሲልክ ''የሴቶችን ልብ የሚያፈራርሰው አሸባሪ በፕሌን ውስጥ'' ብሎ ነበር ጻፈው።

ቼዝ

በአለማቀፍ ውድድሮች አንቱ የተባሉ አሜሪካዊና ኖርዌያዊ የቼዝ ተወዳዳሪዎች ሳይሸናናፉ አንድ ወር አለፋቸው።

አሸናፊው 31 ሚሊዮን ብር የሚያገኝ ሲሆን፤ ጨዋታው ገና ከዚህም በላይ ሊቆይ ይችላል ተብሏል።