418 ኢትዮጵያዊያንን ከየመን ወደ አገር ቤት ማጓጓዝ መጀመሩና ሌሎች አጫጭር ዜናዎች

Image copyright ABDO HYDER

ኢትዮጵያ

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በየመን በጤና ችግር ውስጥ ነበሩ ያላቸውን 418 ኢትዯጵያዊያንን ወደ አገር ቤት ማጓጓዝ ጀመረ።

ከ2005 ወዲህ በየመን አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ሲመለሱ ይሄኛው የመጀመሪያ ነው።

ሌሴቶ

የሌሴቶ ፓርላማ አባላት 100% የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ጠየቁ።

ጭማሪው በሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሁንታን ያገኘ ሲሆን፤ ደመወዛቸው እስከ 5300 ዶላር ከፍ ሊል ይችላል ተብሏል።

". . . ጥፍር መንቀል ሕጋዊ አይደለም ስንለው ብሔሩ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል" ጠ/ሚ ዐብይ

''የአንድ ቤተሰብ አባላት ግድያ'' በቤኒሻንጉል ክልሏ ያሶ ከተማ

ቱኒዚያ

ቱኒዚያውያን የሳዑዲው ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን ወደ ሃገራቸው ሊያደርጉት ያሰቡትን ጉብኝት ተቃውመው ለሁለተኛ ቀን ሰልፍ ወጡ።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ሳዑዲ ውስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሚዲያ ጭቆና አለ ሲሉም ተደምጠዋል።

አሜሪካ

ፍሎሪዳ ውስጥ የሚገኝ አንድ የ18 ዓመት ወጣት የፈጸመው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በበይነ መረብ አማካይነት ተጋለጠ።

ወጣቱ ከጓደኞቹ ጋር በበይነ መረብ በሚያደርጉት ግጥሚያ ላይ በእረፍት ሰዓት አስገድዶ የሚደፈራትን ሴት የድረሱልኝ ጥሪ የሰሙት ጓደኞቹ ለፖሊስ ጠቁመዋል።

አውስትራሊያ

አውስትራሊያ ውስጥ የሚገኝ የአውሮፕላን አብራሪ አየር ላይ እንቅልፍ ወስዶት መዳረሻውን በማለፍ 50 ኪሎሜትር መብረሩ ተገለጸ።

ሰውዬው አውሮፕላኑን እንዴት እንዳሳረፈው ባይገለጽም፤ ምንም አይነት ጉዳት አላደረሰም ተብሏል።

ፈረንሳይ

አንድ የፈረንሳይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊ ለሰሜን ኮሪያ በመሰለልና ሃገራዊ መረጃዎችን በማቀበል ተከሰሱ።

ኃላፊው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ የእሳቸውና የቤተሰባቸው መኖሪያዎች ተፈትሿል ተብሏል።

በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ

"የኖርዌይ ፓስፖርቴን መልሼ ኢትዮጵያዊ መሆን እችላለሁ" አቶ ሌንጮ ለታ

ዓለም

ኤልኒኖ የተባለው ተፈጥሯዊ አደጋ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ሊከሰት እንደሚችል የዓለም አቀፉ የአየር ትንበያ ተቋም አስታወቀ።

ከፓሲፊክ ውቂያኖስ የሚነሳው ሙቅ አየር በደቡብ አሜሪካ፣ አፍሪካና እሲያ ከባድ ጎርፍ ሊያስከትል ይችላል ተብሏል።

***

በዓለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በሕይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው እንደሚገደሉ አንድ ጥናት ጠቆመ።

ጥናቱን የሰራው የተባበሩት መንግስታት ለሴቶች ከቤታቸው የበለጠ አስፈሪ ቦታ የለም ብሏል።